2 ነገሥት 2:22-25
2 ነገሥት 2:22-25 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ነገር ውኃው ከዚያ ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ተፈውሶአል። ከዚያም ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመንገድም ሲወጣ ልጆች ከከተማዪቱ ወጥተው፥ “አንተ ራሰ በራ! ውጣ! አንተ ራሰ በራ! ውጣ” ብለው አፌዙበት። ዘወርም ብሎ አያቸው፤ በእግዚአብሔርም ስም ረገማቸው፤ ወዲያውም ከዱር ሁለት ድቦች ወጥተው ከእነርሱ አርባ ሁለቱን ሰባበሩአቸው። ከዚያም ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሄደ፤ ከዚያም ወደ ሰማርያ ተመለሰ።
2 ነገሥት 2:22-25 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኤልሳዕ እንደ ተናገረውም ውሃው እስከ ዛሬ ድረስ የተፈወሰ ነው። ኤልሳዕም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመንገድ ላይ ሲሄድ ሳለም ልጆች ከከተማ ወጥተው፣ “አንተ መላጣ፤ ውጣ! አንተ መላጣ ውጣ!” እያሉ አፌዙበት። ኤልሳዕም ዘወር ብሎ ተመለከታቸውና በእግዚአብሔር ስም ረገማቸው፤ ከዚያም ሁለት እንስት ድቦች ከዱር ወጥተው ከልጆቹ አርባ ሁለቱን ሰባበሯቸው። እርሱም ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሄደ፤ ከዚያም ወደ ሰማርያ ተመለሰ።
2 ነገሥት 2:22-25 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ነገር ውሃው እስከ ዛሬ ድረስ ተፈውሶአል። ከዚያም ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመንገድም ሲወጣ ብላቴኖች ከከተማይቱ ወጥተው “አንተ መላጣ፥ ውጣ! አንተ መላጣ፥ ውጣ!” ብለው አፌዙበት። ዘወርም ብሎ አያቸው፤ በእግዚአብሔርም ስም ረገማቸው፤ ከዱርም ሁለት ድቦች ወጥተው ከብላቴኖች አርባ ሁለቱን ሰባበሩአቸው። ከዚያም ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሄደ፤ ከዚያም ወደ ሰማርያ ተመለሰ።
2 ነገሥት 2:22-25 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ኤልሳዕ በተናገረው መሠረት ውሃው እስከ ዛሬ ድረስ ንጹሕ ነው። ኤልሳዕም ወደ ቤትኤል ለመሄድ ከኢያሪኮ ተነሣ፤ በመንገድ ሳለ ከከተማይቱ በርከት ያሉ ልጆች ወጥተው ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ “አንተ ራሰ መላጣ ከዚህ ውጣ!” እያሉ ጮኹበት። ኤልሳዕም መለስ ብሎ ዙሪያውን በመቃኘት፥ አተኲሮ ተመለከታቸውና በእግዚአብሔር ስም ረገማቸው፤ በዚህም ጊዜ ሁለት እንስት ድቦች ከጫካ ወጥተው ከእነዚያ ልጆች መካከል አርባ ሁለቱን ሰባብረው ጣሉአቸው። ኤልሳዕም ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣ፤ ዘግየት ብሎ ግን ወደ ሰማርያ ተመለሰ።
2 ነገሥት 2:22-25 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)