የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 2

2
የኤ​ል​ያስ ዕር​ገት
1ከዚ​ህም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኤል​ያ​ስን በዐ​ውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ በሚ​ያ​ወ​ጣው ጊዜ ኤል​ያ​ስና ኤል​ሳዕ ከጌ​ል​ጌላ ተነ​ሥ​ተው ሄዱ። 2ኤል​ያ​ስም ኤል​ሳ​ዕን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ቤቴል ልኮ​ኛ​ልና በዚሁ ቈይ” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ሕያው ነፍ​ስ​ህ​ንም አል​ለ​ይ​ህም” አለው። ወደ ቤቴ​ልም ደረሱ። 3በቤ​ቴ​ልም የነ​በሩ የነ​ቢ​ያት ልጆች ወደ ኤል​ሳዕ መጥ​ተው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጌታ​ህን ከአ​ንተ ለይቶ ዛሬ እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው ዐው​ቀ​ሃ​ልን?” አሉት። እር​ሱም፥ “አዎን፥ ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ ዝም በሉ” አላ​ቸው። 4ኤል​ያ​ስም ኤል​ሳ​ዕን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ኢያ​ሪኮ ልኮ​ኛ​ልና፥ በዚህ ቈይ” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ሕያው ነፍ​ስ​ህ​ንም አል​ለ​ይ​ህም” አለው። 5ወደ ኢያ​ሪ​ኮም ደረሱ፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም የነ​በሩ የነ​ቢ​ያት ልጆች ወደ ኤል​ሳዕ ቀር​በው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጌታ​ህን ከራ​ስህ ላይ ዛሬ እን​ዲ​ወ​ስ​ደው ዐው​ቀ​ሃ​ልን?” አሉት። እር​ሱም፥ “አዎን፥ ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ ዝም በሉ” አላ​ቸው። 6ኤል​ያ​ስም ኤል​ሳ​ዕን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ልኮ​ኛ​ልና እባ​ክህ፥ በዚህ ቈይ” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ሕያው ነፍ​ስ​ህ​ንም አል​ለ​ይ​ህም” አለው፤ ሁለ​ቱም ሄዱ።
7ከነ​ቢ​ያ​ትም ልጆች አምሳ ሰዎች ሄዱ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ርቀው ቆሙ፤ እነ​ዚ​ህም ሁለቱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዳር ቆመው ነበር። 8ኤል​ያ​ስም መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ውን ወስዶ ጠቀ​ለ​ለው፤ የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ውኃ መታ​በት፤ ውኃ​ውም ወዲ​ህና ወዲያ ተከ​ፈለ፤ ሁለ​ቱም በደ​ረቅ ተሻ​ገሩ። ወጥ​ተ​ውም በም​ድረ በዳው ቆሙ። 9ከተ​ሻ​ገ​ሩም በኋላ ኤል​ያስ ኤል​ሳ​ዕን፥ “ከአ​ንተ ሳል​ወ​ሰድ አደ​ር​ግ​ልህ ዘንድ የም​ት​ሻ​ውን ለምን” አለው፤ ኤል​ሳ​ዕም፥ “መን​ፈ​ስህ በእኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለ። 10ኤል​ያ​ስም፥ “አስ​ቸ​ጋሪ ነገር ለም​ነ​ሃል፤ ነገር ግን ከአ​ንተ ዘንድ በተ​ወ​ሰ​ድሁ ጊዜ ብታ​የኝ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ አለ​ዚያ ግን አይ​ሆ​ን​ል​ህም” አለው። 11ሁለ​ቱም እየ​ተ​ነ​ጋ​ገሩ ሲሄዱ፥ እነሆ፥ የእ​ሳት ሰረ​ገ​ላና የእ​ሳት ፈረ​ሶች በሁ​ለቱ መካ​ከል ገብ​ተው ከፈ​ሉ​አ​ቸው፤ ኤል​ያ​ስም በዐ​ውሎ ነፋስ ንው​ጽ​ው​ጽታ ወደ ሰማይ ወጣ።
12ኤል​ሳ​ዕም አይቶ፥ “አባቴ! አባቴ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤል ኀይ​ላ​ቸ​ውና ጽን​ዓ​ቸው፥”#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የእ​ስ​ራ​ኤል ሰረ​ገ​ላ​ቸ​ውና ፈረ​ሰ​ኛ​ቸው” ይላል። ብሎ ጮኸ። ከዚ​ያም ወዲያ ዳግ​መኛ አላ​የ​ውም፤ ልብ​ሱ​ንም ይዞ ከሁ​ለት ቀደ​ደው። 13ኤል​ያ​ስም መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ውን ለኤ​ል​ሳዕ ጣለ​ለት፤ በኤ​ል​ሳ​ዕም ራስ ላይ ዐረፈ። ኤል​ሳ​ዕም ተመ​ልሶ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዳር ቆመ። 14በራሱ ላይ ያረ​ፈ​ች​ውን የኤ​ል​ያ​ስን መጠ​ም​ጠ​ሚያ ወስዶ ውኃ​ውን መታ​ባት፦ ውኃው ግን አል​ተ​ከ​ፈ​ለም፤ እር​ሱም፥ “የኤ​ል​ያስ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዴት ነው? እን​ዴ​ትስ ነው?” አለ። ከዚ​ህም በኋላ ውኃ​ውን በመታ ጊዜ ወዲ​ህና ወዲያ ተከ​ፈለ፤ ኤል​ሳ​ዕም ተሻ​ገረ።
15በኢ​ያ​ሪ​ኮም የነ​በ​ሩት የነ​ቢ​ያት ልጆች ኤል​ሳዕ ወደ እነ​ርሱ ሲመጣ ባዩት ጊዜ፥ “የኤ​ል​ያስ መን​ፈስ በኤ​ል​ሳዕ ላይ ዐር​ፎ​አል” አሉ። ሊገ​ና​ኙ​ትም መጥ​ተው በፊቱ በም​ድር ላይ ሰገ​ዱ​ለት። 16እነ​ር​ሱም፥ “እነሆ፥ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጋር አምሳ ኀ`ያላን ሰዎች አሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ወይም ወደ አንድ ተራራ ወይም ወደ አንድ ኮረ​ብታ ጥሎት እንደ ሆነ፥ ሄደው ጌታ​ህን ይፈ​ል​ጉት” አሉት። ኤል​ሳ​ዕም፥ “አት​ላኩ፤” አላ​ቸው። 17እስ​ኪ​ያ​ፍ​ራ​ቸ​ውም ድረስ ግድ ባሉት ጊዜ፥ “ላኩ” አለ፤ አም​ሳም ሰዎች ላኩ፤ ሦስት ቀንም ፈል​ገው አላ​ገ​ኙ​ትም። 18በኢ​ያ​ሪ​ኮም ተቀ​ምጦ ሳለ ወደ እርሱ ተመ​ለሱ፤ እር​ሱም፥ “አት​ላኩ፥ አት​ሂ​ዱም አላ​ል​ኋ​ች​ሁ​ምን?” አላ​ቸው።
ኤል​ሳዕ ያደ​ረ​ጋ​ቸው ተአ​ም​ራት
19የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሰዎች ኤል​ሳ​ዕን፥ “እነሆ፥ ጌታ​ችን እን​ደ​ም​ታይ የዚች ከተማ ኑሮ መል​ካም ነው፤ ውኃው ግን ክፉ ነው፤ ሴቶ​ችም ሲጠ​ጡት ይመ​ክ​ናሉ፥”#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ምድ​ሪ​ቱም ፍሬ​ዋን ትጨ​ነ​ግ​ፋ​ለች” ይላል። አሉት። 20እር​ሱም፥ “አዲስ ማሰሮ አም​ጡ​ልኝ፤ ጨውም ጨም​ሩ​በት” አለ፤ ያንም አመ​ጡ​ለት። 21ውኃው ወዳ​ለ​በ​ትም ምንጭ ወጥቶ ጨው ጣለ​በ​ትና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህን ውኃ ፈው​ሼ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ህም በኋላ የሚ​ሞት፥ የሚ​መ​ክ​ንም አይ​ኖ​ርም” አለ። 22ኤል​ሳ​ዕም እንደ ተና​ገ​ረው ነገር ውኃው ከዚያ ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ተፈ​ው​ሶ​አል።
23ከዚ​ያም ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመ​ን​ገ​ድም ሲወጣ ልጆች ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጥ​ተው፥ “አንተ ራሰ በራ! ውጣ! አንተ ራሰ በራ! ውጣ” ብለው አፌ​ዙ​በት። 24ዘወ​ርም ብሎ አያ​ቸው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ረገ​ማ​ቸው፤ ወዲ​ያ​ውም ከዱር ሁለት ድቦች ወጥ​ተው ከእ​ነ​ርሱ አርባ ሁለ​ቱን ሰባ​በ​ሩ​አ​ቸው። 25ከዚ​ያም ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ሄደ፤ ከዚ​ያም ወደ ሰማ​ርያ ተመ​ለሰ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ