2 ነገሥት 1:7-8
2 ነገሥት 1:7-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እርሱም፥ “ሊገናኛችሁ የወጣው፦ ይህንስ ቃል የነገራችሁ ሰው መልኩ ምን ይመስላል?” አላቸው። እነርሱም፥ “ሰውዬው ጠጕራም ነው፤ በወገቡም ጠፍር ታጥቆ ነበር” አሉት። እርሱም፥ “ቴስብያዊው ኤልያስ ነው” አላቸው።
2 ነገሥት 1:7-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ንጉሡም፣ “ለመሆኑ ሊገናኛችሁ መጥቶ እንዲህ ያላችሁ ሰው እንዴት ያለ ነው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም “ሰውየው ጠጕራም፣ በወገቡም ጠፍር ታጥቆ ነበር” አሉት። ንጉሡም፣ “ዐወቅሁት፤ ቴስብያዊው ኤልያስ ነው” አላቸው።
2 ነገሥት 1:7-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እርሱም “ሊገናኛችሁ የወጣው፥ ይህንስ ቃል የነገራችሁ ሰው መልኩ ምን ይመስላል?” አላቸው። እነርሱም “ሰውዮው ጠጕራም ነው፤ በወገቡም ጠፍር ታጥቆ ነበር፤” አሉት። እርሱም “ቴስብያዊው ኤልያስ ነው፤” አለ።