2 ዜና መዋዕል 23:16-21
2 ዜና መዋዕል 23:16-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ካህኑ ዮዳሄ ራሱ እንዲሁም ንጉሥ ኢዮአስና ሕዝቡ የእግዚአብሔር ሕዝብ መሆናቸውን ለማደስ ቃል ኪዳን እንዲገቡ አደረገ። ከዚህም በኋላ ሁሉም በአንድነት ባዓል ተብሎ ወደሚጠራው ቤተ ጣዖት ሄደው አፈረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሁሉ ሰባበሩ፤ ማታን ተብሎ የሚጠራውንም የባዓል ካህን በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደሉት። ዮዳሄ ካህናቱንና ሌዋውያኑን የቤተ መቅደሱ ሥራ ኀላፊዎች እንዲሆኑ አደረገ፤ የእነርሱም ተግባር በንጉሥ ዳዊት የተመደበላቸውን ሥራ ማከናወንና በኦሪት ሕግ መሠረት ለእግዚአብሔር የሚቀርቡትን መሥዋዕት ማቃጠል ነበር፤ እንዲሁም በዳዊት መመሪያ መሠረት የዜማና የበዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት ኀላፊነት ተሰጥቶአቸው ነበር፤ ዮዳሄ ያልነጻ ማንኛውም ሰው ወደ ቤተ መቅደስ እንዳይገባ በቤተ መቅደሱ ቅጽር በሮች ሆነው የሚጠብቁ ዘበኞችን መድቦ ነበር። የጦር መኰንኖቹ፥ የታወቁ የአገር ሽማግሌዎች የመንግሥት ባለሥልጣኖችና የቀሩትም ሕዝብ ሁሉ ከዮዳሄ ጋር በመሆን ከቤተ መቅደስ እስከ ቤተ መንግሥት ድረስ ንጉሡን አጅበው ሄዱ፤ በቤተ መንግሥቱም ዋና በር ገቡ፤ ንጉሡም በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በታላቅ ደስታ ተሞሉ፤ ዐታልያም ተገድላ ስለ ነበር ከተማይቱ ሰላም ሰፍኖባት ጸጥ ብላ ነበር።
2 ዜና መዋዕል 23:16-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ዮዳሄም ራሱ፣ ሕዝቡና ንጉሡ የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ ቃል ኪዳን እንዲገቡ አደረገ። ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ሄደው የበኣልን ቤተ ጣዖት አፈራረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሰባበሩ፤ የበኣልን ካህን ማታንንም በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደሉት። ዮዳሄም በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈውና ዳዊትም እንዳዘዘው፣ በደስታና በመዝሙር የሚቃጠለውን የእግዚአብሔርን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ዳዊት ለመደባቸው ካህናትና ሌዋውያን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ኀላፊነት ሰጣቸው። እንዲሁም በማንኛውም ነገር የረከሰ ሰው እንዳይገባ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅጥር በሮች ላይ ጠባቆች አቆመ። የመቶ አለቆቹን፣ መኳንንቱን፣ የሕዝቡን ገዦችና የአገሩን ሕዝብ ሁሉ ይዞ ንጉሡን ከላይ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወደ ታች አመጣው። በላይኛውም መግቢያ በኩል ወደ ቤተ መንግሥቱ ገብተው ንጉሡን በመንግሥቱ ዙፋን ላይ አስቀመጡት። መላውም የአገሩ ሕዝብ ተደሰተ፤ ጎቶልያ በሰይፍ ስለ ተገደለች ከተማዪቱ ጸጥ አለች።
2 ዜና መዋዕል 23:16-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ካህኑ ኢዮአዳም በእርሱና በሕዝቡ ሁሉ፥ በንጉሡም መካከል የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ ቃል ኪዳን አደረገ። የሀገሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በዓል ቤት ሄደው አፈረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹንም አደቀቁ፤ የበዓልንም ካህን ማታንን በመሠዊያው ፊት ገደሉት። ካህኑ ኢዮአዳም በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈው እንደ ዳዊት ትእዛዝ በደስታና በመዝሙር ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ ዳዊት በእግዚአብሔር ቤት የከፈላቸውን ካህናትና ሌዋውያን በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ላይ ሾመ። በማናቸውም ነገር ሁሉ ርኩስ የሆነ ሰው እንዳይገባ በእግዚአብሔር ቤት በር በረኞችን አኖረ። የመቶ አለቆችንም፥ ከበርቴዎችንም፥ የሕዝቡንም አለቆች፥ የሀገሩንም ሕዝብ ሁሉ ወሰደ፤ ንጉሡንም ከእግዚአብሔር ቤት አወረዱት፤ በእግዚአብሔርም ቤት በውስጠኛው በር በኩል ወደ ንጉሡ ቤት አመጡት፤ ንጉሡንም በመንግሥቱ ዙፋን ላይ አስቀመጡት። የሀገሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ አላቸው፤ ከተማዪቱም ጸጥ አለች፤ ጎቶልያንም በሰይፍ ገደሉአት።
2 ዜና መዋዕል 23:16-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ዮዳሄም ራሱ፣ ሕዝቡና ንጉሡ የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ ቃል ኪዳን እንዲገቡ አደረገ። ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ሄደው የበኣልን ቤተ ጣዖት አፈራረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሰባበሩ፤ የበኣልን ካህን ማታንንም በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደሉት። ዮዳሄም በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈውና ዳዊትም እንዳዘዘው፣ በደስታና በመዝሙር የሚቃጠለውን የእግዚአብሔርን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ዳዊት ለመደባቸው ካህናትና ሌዋውያን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ኀላፊነት ሰጣቸው። እንዲሁም በማንኛውም ነገር የረከሰ ሰው እንዳይገባ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅጥር በሮች ላይ ጠባቆች አቆመ። የመቶ አለቆቹን፣ መኳንንቱን፣ የሕዝቡን ገዦችና የአገሩን ሕዝብ ሁሉ ይዞ ንጉሡን ከላይ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወደ ታች አመጣው። በላይኛውም መግቢያ በኩል ወደ ቤተ መንግሥቱ ገብተው ንጉሡን በመንግሥቱ ዙፋን ላይ አስቀመጡት። መላውም የአገሩ ሕዝብ ተደሰተ፤ ጎቶልያ በሰይፍ ስለ ተገደለች ከተማዪቱ ጸጥ አለች።
2 ዜና መዋዕል 23:16-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ዮዳሄም በእርሱና በሕዝቡ ሁሉ በንጉሡም መካከል የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ ቃል ኪዳን አደረገ። ሕዝቡም ሁሉ ወደ ባኣል ቤት ሄደው አፈረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹንም አደቀቁ፤ የባኣልንም ካህን ማታንን በመሠዊያው ፊት ገደሉት። ዮዳሄም በሙሴ ሕግ እንደተጻፈው፥ እንደ ዳዊትም ትእዛዝ፥ በደስታና በመዝሙር ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ ዳዊት በእግዚአብሔር ቤት የከፈላቸውን ካህናትና ሌዋውያን በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ላይ ሾመ። በማናቸውም ነገር ሁሉ ርኩስ የሆነ ሰው እንዳይገባ በእግዚአብሔር ቤት በር በረኞችን አኖረ። የመቶ አለቆችንም፥ ከበርቴዎቹንም፥ የሕዝቡንም አለቆች፥ የአገሩንም ሕዝብ ሁሉ ወሰደ፤ ንጉሡንም ከእግዚአብሔር ቤት አወረደ፤ በላይኛውም በር በኩል ወደ ንጉሡ ቤት መጡ፤ ንጉሡንም በመንግሥቱ ዙፋን ላይ አኖሩት። የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ አላቸው፤ ከተማይቱም ጸጥ አለች፤ ጎቶሊያንም በሰይፍ ገደሉአት።
2 ዜና መዋዕል 23:16-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ካህኑ ዮዳሄ ራሱ እንዲሁም ንጉሥ ኢዮአስና ሕዝቡ የእግዚአብሔር ሕዝብ መሆናቸውን ለማደስ ቃል ኪዳን እንዲገቡ አደረገ። ከዚህም በኋላ ሁሉም በአንድነት ባዓል ተብሎ ወደሚጠራው ቤተ ጣዖት ሄደው አፈረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሁሉ ሰባበሩ፤ ማታን ተብሎ የሚጠራውንም የባዓል ካህን በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደሉት። ዮዳሄ ካህናቱንና ሌዋውያኑን የቤተ መቅደሱ ሥራ ኀላፊዎች እንዲሆኑ አደረገ፤ የእነርሱም ተግባር በንጉሥ ዳዊት የተመደበላቸውን ሥራ ማከናወንና በኦሪት ሕግ መሠረት ለእግዚአብሔር የሚቀርቡትን መሥዋዕት ማቃጠል ነበር፤ እንዲሁም በዳዊት መመሪያ መሠረት የዜማና የበዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት ኀላፊነት ተሰጥቶአቸው ነበር፤ ዮዳሄ ያልነጻ ማንኛውም ሰው ወደ ቤተ መቅደስ እንዳይገባ በቤተ መቅደሱ ቅጽር በሮች ሆነው የሚጠብቁ ዘበኞችን መድቦ ነበር። የጦር መኰንኖቹ፥ የታወቁ የአገር ሽማግሌዎች የመንግሥት ባለሥልጣኖችና የቀሩትም ሕዝብ ሁሉ ከዮዳሄ ጋር በመሆን ከቤተ መቅደስ እስከ ቤተ መንግሥት ድረስ ንጉሡን አጅበው ሄዱ፤ በቤተ መንግሥቱም ዋና በር ገቡ፤ ንጉሡም በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በታላቅ ደስታ ተሞሉ፤ ዐታልያም ተገድላ ስለ ነበር ከተማይቱ ሰላም ሰፍኖባት ጸጥ ብላ ነበር።
2 ዜና መዋዕል 23:16-21 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ዮዳሄም በእርሱና በሕዝቡ ሁሉ በንጉሡም መካከል የጌታ ሕዝብ እንዲሆኑ ቃል ኪዳን አደረገ። ሕዝቡም ሁሉ ወደ ባዓል ቤት ሄደው አፈረሱት፥ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹንም አደቀቁ፥ የባዓልንም ካህን ማታንን በመሠዊያው ፊት ገደሉት። ዮዳሄም በሙሴ ሕግ እንደተጻፈው፥ እንደ ዳዊትም ትእዛዝ፥ በደስታና በመዝሙር ለጌታ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ዳዊት በጌታ ቤት የከፈላቸውን ካህናትና ሌዋውያን በጌታ ቤት አገልግሎት ላይ ሾመ። በማናቸውም ነገር ሁሉ ርኩስ የሆነ ሰው እንዳይገባ በጌታ ቤት በር በጠባቂዎችን አኖረ። የመቶ አለቆችንም፥ ከበርቴዎቹንም፥ የሕዝቡንም አለቆች፥ የአገሩንም ሕዝብ ሁሉ ወሰደ፥ ንጉሡንም ከጌታ ቤት ወስደው በላይኛው በር በኩል ወደ ንጉሡ ቤት መጡ፥ ንጉሡንም በመንግሥቱ ዙፋን ላይ አስቀመጡት። የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ አላቸው፥ ከተማይቱም ጸጥ አለች፤ ጎቶሊያንም በሰይፍ ገደሉአት።