1 ነገሥት 16:1-20

1 ነገሥት 16:1-20 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ስለ ባኦስ እን​ዲህ ብሎ ወደ አናኒ ልጅ ወደ ኢዩ መጣ። “እኔ ከመ​ሬት አን​ሥቼ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ አንተ ግን በከ​ንቱ ጣዖ​ታ​ቸው ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን በአ​ሳ​ታ​ቸው በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መን​ገድ ሄድህ፤ ስለ​ዚ​ህም፥ እነሆ፥ ባኦ​ስ​ንና ቤቱን ፈጽሜ አጠ​ፋ​ለሁ፤ ቤት​ህ​ንም እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ቤት አደ​ር​ጋ​ለሁ። ከባ​ኦ​ስም ወገን በከ​ተ​ማ​ዪቱ ውስጥ የሚ​ሞ​ተ​ውን ውሾች ይበ​ሉ​ታል፤ በሜ​ዳ​ውም የሚ​ሞ​ተ​ውን የሰ​ማይ ወፎች ይበ​ሉ​ታል።” የቀ​ረ​ውም የባ​ኦስ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሁሉ፥ ኀይ​ሉም ሁሉ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ ነው። ባኦ​ስም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በቴ​ር​ሳም ተቀ​በረ፤ ልጁም ኤላ በአሳ በሃያ ስድ​ስ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በፋ​ን​ታው ነገሠ። በእ​ጁም ሥራ ያስ​ቈ​ጣው ዘንድ፥ እንደ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ቤት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስላ​ደ​ረ​ገው ክፋት ሁሉ እር​ሱ​ንም ስለ ገደ​ለው፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በባ​ኦ​ስና በቤቱ ላይ ወደ አናኒ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢዩ መጣ። የባ​ኦ​ስም ልጅ ኤላ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በቴ​ርሳ ሁለት ዓመት ነገሠ። የእ​ኩ​ሌ​ቶቹ ፈረ​ሶች አለቃ ዘም​ሪም አሽ​ከ​ሮ​ቹን ሁሉ ሰብ​ስቦ ዐመፀ፤ ኤላም በቴ​ርሳ ነበረ፤ በቴ​ር​ሳም በነ​በ​ረው በመ​ጋ​ቢው በአሳ ቤት ይሰ​ክር ነበር። በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በአሳ በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት ዘምሪ ገብቶ ወጋና ገደ​ለው፤ በፋ​ን​ታ​ውም ነገሠ። ከነ​ገ​ሠና በዙ​ፋ​ኑም ከተ​ቀ​መጠ በኋላ፥ የባ​ኦ​ስን ቤት ሁሉ አጠፋ፤ አንድ ወንድ እንኳ አላ​ስ​ቀ​ረ​ለ​ትም። በነ​ቢዩ በኢዩ አፍ በባ​ኦስ ቤት ላይ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ ባኦ​ስና ልጁ ኤላ ስለ ሠሩት ኀጢ​አት ሁሉ፥ በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸው የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያስ​ቈ​ጡት ዘንድ እስ​ራ​ኤ​ልን ስለ አሳ​ቱ​በት ኀጢ​አት፥ ዘምሪ የባ​ኦ​ስን ቤት ሁሉ እን​ዲሁ አጠፋ። የቀ​ረ​ውም የኤላ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ ነው። በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በአሳ በሃያ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመት ዘምሪ በቴ​ርሳ ሰባት ቀን ነገሠ። የእ​ስ​ራ​ኤል ሠራ​ዊት ግን በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሀገር በገ​ባ​ቶን ሰፍ​ረው ነበር። በሰ​ፈር ያሉ ሕዝ​ቡም “ዘምሪ ከድቶ ኤላን ገደ​ለው፥ በፋ​ን​ታ​ውም ነገሠ” ሲሉ ሰሙ። እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በዚያ ቀን በሰ​ፈሩ ውስጥ የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለቃ ዘን​በ​ሪን አነ​ገሡ። ዘን​በ​ሪም ከእ​ርሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከገ​ባ​ቶን ወጥ​ተው ቴር​ሳን ከበቡ። በእ​ር​ስ​ዋም ተቀ​መጡ። ዘም​ሪም ከተ​ማ​ዪቱ እንደ ተያ​ዘች ባየ ጊዜ ወደ ንጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ገባ፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤት በራሱ ላይ በእ​ሳት አቃ​ጠለ፤ ሞተም። ስላ​ደ​ረ​ገ​ውም ኀጢ​አት፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስላ​ሳ​ተ​በት ኀጢ​አት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አድ​ር​ጎ​አ​ልና፥ በና​ባጥ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም መን​ገድ ሄዶ​አ​ልና ሞተ። የቀ​ረ​ውም የዘ​ምሪ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ዐመፅ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ ነው።

1 ነገሥት 16:1-20 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል በባኦስ ላይ እንዲህ ሲል ወደ አናኒ ልጅ ወደ ኢዩ መጣ፤ “ከትቢያ አንሥቼ፣ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግሁህ፤ አንተ ግን በኢዮርብዓም መንገድ ሄድህ፤ ሕዝቤ እስራኤል ኀጢአት እንዲሠራ፣ በኀጢአቱም ለቍጣ እንዲያነሣሣኝ አሳሳትኸው። ስለዚህ ባኦስንና ቤቱን ፈጽሜ አጠፋለሁ፤ ቤትህንም እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮርብዓም ቤት አደርገዋለሁ። በከተማዪቱ ውስጥ የሚሞቱትን የባኦስን ወገኖች ሁሉ ውሾች ይበሏቸዋል፤ በገጠር የሚሞቱትንም ሁሉ የሰማይ አሞሮች ይቀራመቷቸዋል።” በባኦስ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው፣ ሌላው ያደረገው ሥራው በሙሉ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? ባኦስ፣ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በቴርሳም ተቀበረ። ልጁም ኤላ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። ከዚህም በቀር የእግዚአብሔር ቃል በአናኒ ልጅ፣ በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባኦስና በቤቱ ላይ የመጣበት ምክንያት፣ በእጁ ሥራ ያስቈጣው ዘንድ እንደ ኢዮርብዓም ቤት ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራን ሁሉ በማድረጉና ኢዮርብዓምን በማጥፋቱም ጭምር ነው። የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሃያ ስድስተኛው ዓመት የባኦስ ልጅ ኤላ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ በቴርሳ ተቀምጦም ሁለት ዓመት ገዛ። ከሹማምቱ አንዱና የግማሽ ሠረገሎቹ አዛዥ የሆነው ዘምሪ ዐምፆ ተነሣበት፤ በዚያ ጊዜ ኤላ በቴርሳ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በሆነው በአርጻ ቤት ጠጥቶ ሰክሮ ነበር፤ ዘምሪም ገብቶ ኤላን ገደለው፤ እርሱም በኤላ እግር ተተክቶ፣ የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ነገሠ። ዘምሪ ወዲያው እንደ ነገሠና በዙፋን እንደ ተቀመጠ፣ የባኦስን ቤተ ሰብ በሙሉ ገደለ፤ የሥጋ ዘመድም ሆነ ወዳጅ አንድም ወንድ አላስቀረም። በዚህ ሁኔታም በነቢዩ በኢዩ አማካይነት በባኦስ ላይ በተነገረው በእግዚአብሔር ቃል መሠረት፣ የባኦስን ቤተ ሰብ ሁሉ ፈጀ። ይህም የሆነው ባኦስና ልጁ ኤላ፣ በማይረቡ ጣዖቶቻቸው ምክንያት የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ያስቈጡት ዘንድ በሠሩት ኀጢአት ሁሉና፣ እስራኤልም እንዲሠሩ በማድረጉ ነበር። ሌላው ኤላ በዘመኑ የፈጸመውና ያደረገው ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ዘምሪ በቴርሳ ሆኖ ሰባት ቀን ብቻ ገዛ። በዚህ ጊዜ ሰራዊቱ የፍልስጥኤማውያን ከተማ የሆነችውን ገባቶንን ከብቦ ሰፍሮ ነበር። በዚያም ሰፈር የነበሩ እስራኤላውያን ዘምሪ ዐምፆ ንጉሡን መግደሉን እንደ ሰሙ፣ የሰራዊቱን አዛዥ ዖምሪን በዚያ ዕለት እዚያው ሰፈር ውስጥ በእስራኤል ላይ ማንገሣቸውን ዐወጁ። ከዚያም ዖምሪና ዐብረውት ያሉት እስራኤላውያን ሁሉ ከገባቶን ወደ ላይ ወጥተው ቴርሳን ከበቡ። ዘምሪ ከተማዪቱ መያዟን ሲያይ፣ ቤተ መንግሥቱ ውስጥ ወዳለው ግንብ ገብቶ በቤተ መንግሥቱ ላይ እሳት ለቀቀበትና በዚሁ ሞተ። ይህ የሆነውም በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ክፉ ሥራ በመሥራትና በኢዮርብዓም መንገድ በመሄድ፣ እንዲሁም ራሱ በሠራው ኀጢአትና እስራኤልም እንዲሠሩ ባደረገው ኀጢአት ምክንያት ነው። ሌላው ዘምሪ በዘመኑ የፈጸመው ድርጊትና ያካሄደውም ዐመፅ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?

1 ነገሥት 16:1-20 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የእግዚአብሔርም ቃል በባኦስ ላይ እንዲህ ብሎ ወደ አናኒ ልጅ ወደ ኢዩ መጣ። እኔ ከመሬት አስነሥቼ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ አድርጌሃለሁ፤ አንተ ግን በኢዮርብዓም መንገድ ሄደሃል፤ በኀጢአታቸውም ያስቆጡኝ ዘንድ ሕዝቤን እስራኤልን አስተሃቸዋል። ስለዚህም፥ እነሆ፥ ባኦስንና ቤቱን ፈጽሜ እጠርጋለሁ፤ ቤትህንም እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮርብዓም ቤት አደርጋለሁ። ከባኦስም ወገን በከተማይቱ ውስጥ የሚሞተውን ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳውም የሚሞተውን የሰማይ ወፎች ይበሉታል። የቀረውም የባኦስ ነገር፥ ሥራውና ጭከናውም፥ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ባኦስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በቴርሳም ተቀበረ፤ ልጁም ኤላ በፋንታው ነገሠ። በእጁም ሥራ ያስቆጣው ዘንድ፥ እንደ ኢዮርብዓም ቤት በእግዚአብሔር ፊት ስላደረገው ክፋት ሁሉ እርሱንም ስለ ገደለው፥ የእግዚአብሔር ቃል በባኦስና በቤቱ ላይ ወደ አናኒ ልጅ ወደ ነቢዩ ወደ ኢዩ መጣ። በይሁዳም ንጉሥ በአሳ በኻያ ስድስተኛው ዓመት የባኦስ ልጅ ኤላ በእስራኤል ላይ በቴርሳ ሁለት ዓመት ነገሠ። የእኩሌቶቹም ሠረገሎች አለቃ ዘምሪ ተማማለበት፤ ኤላም በቴርሳ ነበረ፤ በቴርሳም በነበረው በቤት አሽከሮች አለቃ በአሳ ቤት ይሰክር ነበር። በይሁዳም ንጉሥ በአሳ በኻያ ሰባተኛው ዓመት ዘምሪ ገብቶ መታው፤ ገደለውም፤ በፋንታውም ነገሠ። ንጉሥም በሆነ ጊዜ፥ በዙፋኑም በተቀመጠ ጊዜ፥ የባኦስን ቤት ሁሉ መታ፤ ከዘመዶችና ከወዳጆች ሁሉ አንድ ወንድ እንኳ አልቀረም። ባኦስና ልጁ ኤላ ስለ ሠሩት ኀጢአት ሁሉ፥ በምናምንቴም ሥራቸው የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ያስቆጡት ዘንድ እስራኤልን ስለ አሳቱበት ኀጢአት፥ በነቢዩ በኢዩ አማካይነት በባኦስ ላይ እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ዘምሪ የባኦስን ቤት ሁሉ እንዲሁ አጠፋ። የቀረውም የኤላ ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? በይሁዳ ንጉሥ በአሳ በኻያ ሰባተኛው ዓመት ዘምሪ በቴርሳ ሰባት ቀን ነገሠ። ሕዝቡም በፍልስጥኤም አገር የነበረው ገባቶንን ከብበው ነበር። ከተማይቱንም ከብበው የነበሩ ሕዝብ ዘምሪ እንደ ዐመፀ፥ ንጉሡንም እንደ ገደለ ሰሙ፤ እስራኤልም ሁሉ በዚያ ቀን በሰፈሩ ውስጥ የሠራዊቱን አለቃ ዖምሪን አነገሡ። ዖምሪም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከገባቶን ወጥተው ቴርሳን ከበቡ። ዘምሪም ከተማይቱ እንደ ተያዘች ባየ ጊዜ ወደ ንጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ገባ፤ የንጉሡንም ቤት በራሱ ላይ በእሳት አቃጠለ፤ ስላደረገውም ኀጢአት፥ እስራኤልንም ስላሳተበት ኀጢአት፥ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አድርጎአልና፥ በኢዮርብዓምም መንገድ ሄዶአልና ሞተ። የቀረውም የዘምሪ ነገር፥ ያደረገውም ዐመፅ፥ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?

1 ነገሥት 16:1-20 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የሐናኒ ልጅ በሆነው በነቢዩ ኢዩ አማካይነት እግዚአብሔር ስለ ባዕሻ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ “እኔ ግን ከትቢያ አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግሁህ፤ ታዲያ አንተ እንደ ኢዮርብዓም ኃጢአት ሠራህ፤ ሕዝቤንም ወደ ኃጢአት መራህ፤ የኃጢአታቸውም ብዛት የእኔን ቊጣ አነሣሥቶአል፤ ስለዚህም ኢዮርብዓምን እንዳስወገድኩ አንተንና ቤተሰብህንም አስወግዳለሁ። በከተማይቱ ውስጥ የሚሞተውን ማንኛውንም የቤተሰብህን አባል ውሾች ይበሉታል፤ በየገጠሩም ሜዳ ላይ የሚሞተውን አሞራዎች ይበሉታል።” ባዕሻ ያደረገው ሌላው ነገርና የጀግንነት ሥራዎቹም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፤ ባዕሻ ሞተ፤ በቲርጻም ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኤላ ነገሠ። እግዚአብሔር በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባዕሻና በቤተሰቡ ላይ ያን የትንቢት ቃል የተናገረበት ምክንያት፥ ባዕሻ በፈጸመው ኃጢአት እግዚአብሔርን ስላሳዘነ ነበር፤ ባዕሻ እግዚአብሔርን ያስቈጣውም ከእርሱ ፊት የነበረው ንጉሥ ባደረገው ዐይነት ስለ ሠራው ክፉ ነገር ብቻ ሳይሆን የኢዮርብዓምንም ቤተሰብ ሁሉ በመግደሉ ጭምር ነው። አሳ በይሁዳ በነገሠ በሃያ ስድስተኛው ዓመት የባዕሻ ልጅ ኤላ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ መኖሪያውንም በቲርጻ አድርጎ ሁለት ዓመት ገዛ። የሠረገላዎቹ እኩሌታ ኀላፊ የሆነ ዚምሪ ተብሎ የሚጠራ ከጦር መኰንኖቹ አንዱ በንጉሡ ላይ ዐደመ፤ አንድ ቀን ኤላ በቲርጻ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በሆነው አርጻ ተብሎ በሚጠራው ባለሟሉ ቤት ብዙ መጠጥ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር። በዚህን ጊዜ ዚምሪ ወደዚያ ቤት ሰተት ብሎ ገብቶ ኤላን ገደለው፤ እርሱም በኤላ እግር ተተክቶ ነገሠ፤ ይህም የሆነው የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ነበር። ዚምሪ እንደ ነገሠ ወዲያውኑ የባዕሻ ቤተሰብ አባላት የሆኑትን በሙሉ ገደለ፤ የባዕሻ ዘመድና ወዳጅ የሆነውን ወንድ ሁሉ በሞት ቀጣ። በዚህም ዐይነት እግዚአብሔር በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባዕሻ ላይ ባናገረው ትንቢት መሠረት ዚምሪ የባዕሻን ቤተሰብ በሙሉ ፈጀ። ይህም የሆነበት ምክንያት ባዕሻና ልጁ ኤላ ጣዖት በማምለካቸውና የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ኃጢአት በመምራታቸው የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቊጣ በማነሣሣታቸው ነው። ኤላ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል። አሳ በይሁዳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ዚምሪ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በቲርጻ አድርጎ በእስራኤል ላይ ሰባት ቀን ብቻ ነገሠ፤ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ወታደሮች በፍልስጥኤም የምትገኘውን የጊበቶንን ከተማ ከበው ነበር። ዚምሪ ዐምፆ ንጉሡን መግደሉን በሰሙ ጊዜ በዚያው እንዳሉ ወዲያውኑ የጦር አዛዣቸው የነበረውን ዖምሪን አነገሡ። ዖምሪና ወታደሮቹ የጊበቶንን ከበባ አቆሙ፤ ከዚያም ገሥግሠው ሄደው ቲርጻን ከበቡ፤ ዚምሪ ከተማይቱ እንደ ተያዘች ባየ ጊዜ በቤተ መንግሥቱ ውስጠኛ ክፍል ወዳለው ምሽግ ውስጥ ገብቶ በቤተ መንግሥቱ ላይ እሳት ለቀቀበት፤ እርሱም በእሳት ነበልባል ተቃጥሎ ሞተ። ይህ የሆነበት ምክንያት በሠራው ኃጢአት እግዚአብሔርን በማሳዘኑ ነው፤ እርሱ ራሱ በሠራው ኃጢአትና እስራኤልንም ወደ ኃጢአት በመምራቱ ምክንያት ከእርሱ በፊት እንደ ነበረው እንደ ኢዮርብዓም እግዚአብሔርን አስቈጥቶአል። ዚምሪ የሠራው ሌላው ነገር ሁሉና ያደረገውም ሤራ ጭምር በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።

1 ነገሥት 16:1-20 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የሐናኒ ልጅ በሆነው በነቢዩ ኢዩ አማካይነት ጌታ ስለ ባዕሻ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ “እኔ ግን ከትቢያ አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግሁህ፤ ታዲያ አንተ እንደ ኢዮርብዓም ኃጢአት ሠራህ፤ ሕዝቤንም ወደ ኃጢአት መራህ፤ የኃጢአታቸውም ብዛት የእኔን ቁጣ አነሣሥቶአል። ስለዚህም ኢዮርብዓምን እንዳስወገድኩ አንተንና ቤተሰብህንም አስወግዳለሁ። በከተማይቱ ውስጥ የሚሞተውን ማንኛውንም የቤተሰብህን አባል ውሾች ይበሉታል፤ በየገጠሩም ሜዳ ላይ የሚሞተውን አሞራዎች ይበሉታል።” ባዕሻ ያደረገው ሌላው ነገርና የጀግንነት ሥራዎቹም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል። ባዕሻ ሞተ፤ በቲርጻም ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኤላ ነገሠ። ጌታ በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባዕሻና በቤተሰቡ ላይ ያን የትንቢት ቃል የተናገረበት ምክንያት፥ ባዕሻ በፈጸመው ኃጢአት ጌታን ስላሳዘነ ነበር፤ ባዕሻ ጌታን ያስቆጣውም ከእርሱ ፊት የነበረው ንጉሥ ባደረገው ዓይነት ስለ ሠራው ክፉ ነገር ብቻ ሳይሆን የኢዮርብዓምንም ቤተሰብ ሁሉ በመግደሉ ጭምር ነው። አሳ በይሁዳ በነገሠ በሃያ ስድስተኛው ዓመት የባዕሻ ልጅ ኤላ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ መኖሪያውንም በቲርጻ አድርጎ ሁለት ዓመት ገዛ። የሠረገላዎቹ እኩሌታ ኀላፊ የሆነ ዚምሪ ተብሎ የሚጠራ ከጦር መኰንኖቹ አንዱ በንጉሡ ላይ ዐደመ፤ አንድ ቀን ኤላ በቲርጻ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በሆነው አርጻ ተብሎ በሚጠራው ባለሟሉ ቤት ብዙ መጠጥ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር። በዚህ ጊዜ ዚምሪ ወደዚያ ቤት ሰተት ብሎ ገብቶ ኤላን ገደለው፤ እርሱም በኤላ እግር ተተክቶ ነገሠ፤ ይህም የሆነው የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ነበር። ዚምሪ እንደ ነገሠ ወዲያውኑ የባዕሻ ቤተሰብ አባላት የሆኑትን በሙሉ ገደለ፤ የባዕሻ ዘመድና ወዳጅ የሆነውን ወንድ ሁሉ በሞት ቀጣ። በዚህም ዓይነት ጌታ በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባዕሻ ላይ ባናገረው ትንቢት መሠረት ዚምሪ የባዕሻን ቤተሰብ በሙሉ ፈጀ። ይህም የሆነበት ምክንያት ባዕሻና ልጁ ኤላ ጣዖት በማምለካቸውና የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ኃጢአት በመምራታቸው የእስራኤልን አምላክ የጌታን ቁጣ በማነሣሣታቸው ነው። ኤላ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል። አሳ በይሁዳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ዚምሪ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በቲርጻ አድርጎ በእስራኤል ላይ ሰባት ቀን ብቻ ነገሠ፤ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ወታደሮች በፍልስጥኤም የምትገኘውን የጊበቶንን ከተማ ከበው ነበር። ዚምሪ ዐምፆ ንጉሡን መግደሉን በሰሙ ጊዜ በዚያው እንዳሉ ወዲያውኑ የጦር አዛዣቸው የነበረውን ዖምሪን አነገሡ። ዖምሪና ወታደሮቹ የጊበቶንን ከበባ አቆሙ፤ ከዚያም ገሥግሠው ሄደው ቲርጻን ከበቡ። ዚምሪ ከተማይቱ እንደ ተያዘች ባየ ጊዜ በቤተ መንግሥቱ ውስጠኛ ክፍል ወዳለው ምሽግ ውስጥ ገብቶ በቤተ መንግሥቱ ላይ እሳት ለቀቀበት፤ እርሱም በእሳት ነበልባል ተቃጥሎ ሞተ። ይህ የሆነበት ምክንያት በሠራው ኃጢአት ጌታን በማሳዘኑ ነው፤ እርሱ ራሱ በሠራው ኃጢአትና እስራኤልንም ወደ ኃጢአት በመምራቱ ምክንያት ከእርሱ በፊት እንደነበረው እንደ ኢዮርብዓም ጌታን አስቆጥቶአል። ዚምሪ የሠራው ሌላው ነገር ሁሉና ያደረገውም ሤራ ጭምር በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።