1 ቆሮንቶስ 4:1-13
1 ቆሮንቶስ 4:1-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እንግዲህ ሰው ሁሉ እኛን እንደ ክርስቶስ አገልጋዮችና እንደ እግዚአብሔር ምስጢር ባለዐደራዎች ሊቈጥረን ይገባል። ባለዐደራዎችም ታማኝ ሆነው መገኘት አለባቸው። በእናንተም ሆነ በሰዎች የፍርድ ሸንጎ ቢፈረድብኝ እኔ በበኩሌ ግድ የለኝም፤ እኔ እንኳ በራሴ ላይ አልፈርድም። ኅሊናዬ ንጹሕ ነው፤ ይህ ግን ጥፋት አልባ መሆኔን አያረጋግጥም፤ በእኔ ላይ የሚፈርድ ጌታ ነው። ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ በምንም ነገር አትፍረዱ፤ ጌታ እስኪመጣ ጠብቁ። እርሱ በጨለማ ውስጥ የተሰወረውን ወደ ብርሃን ያመጣዋል፤ በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውንም ሐሳብ ይገልጠዋል። በዚያ ጊዜ እያንዳንዱ ሰው የሚገባውን ምስጋና ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል። እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ለእናንተ ጥቅም ብዬ በዚህ ጕዳይ እኔን ራሴንና አጵሎስን ምሳሌ አድርጌ አቅርቤላችኋለሁ፤ ይህንም ያደረግሁት፣ “ከተጻፈው አትለፍ” የሚለውን ከእኛ እንድትማሩ ነው። ስለዚህ አንዱን ሰው ከሌላው አብልጣችሁ አትመኩበት። ለመሆኑ፣ አንተን ከሌላው እንድትበልጥ ያደረገህ ማን ነው? ያልተቀበልኸው የራስህ የሆነ ነገር ምን አለ? ከተቀበልህ ታዲያ፣ እንዳልተቀበልህ ለምን ትመካለህ? አሁንስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝታችኋል! ሀብታምም ሆናችኋል! ከእኛም ተለይታችሁ ነግሣችኋል! በርግጥ ብትነግሡማ እኛም ከእናንተ ጋራ በነገሥን ነበር፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን፣ ሞት እንደ ተፈረደባቸው ሰዎች ከሰው ሁሉ መጨረሻ ያሰለፈን ይመስለኛል፤ ለዓለም ሁሉ፣ ለመላእክትም ለሰዎችም ትርኢት ሆነናል። እኛ ስለ ክርስቶስ ብለን ሞኞች ነን፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ጥበበኞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ናችሁ፤ እናንተ የተከበራችሁ ናችሁ፤ እኛ ግን የተዋረድን ነን። እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፤ እንጠማለን፤ እንራቈታለን፤ እንደበደባለን፤ ያለ መጠለያ እንንከራተታለን፤ በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲረግሙን እንመርቃለን፤ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፤ ስማችንን ሲያጠፉ መልካም እንመልሳለን፤ እስከ አሁንም ድረስ የዓለም ጕድፍ፣ የምድር ጥራጊ ሆነናል።
1 ቆሮንቶስ 4:1-13 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እንግዲህ ሰው ሁሉ እኛን የክርስቶስ አገልጋዮች እንደ ሆንን የእግዚአብሔርንም ምሥጢር የመግለጥ ኀላፊነት የተሰጠን ባለ ዐደራዎች እንደ ሆንን አድርጎ ሊቈጥረን ይገባል። ባለ ዐደራዎችም ታማኞች ሆነው መገኘት አለባቸው። ስለ እኔ የሆነ እንደ ሆነ እናንተም ብትፈርዱብኝ ወይም ሌላ ሰው ቢፈርድብኝ ምንም ግድ የለኝም፤ በእውነቱ እኔ በራሴ ላይ እንኳ መፍረድ አልችልም። እኔ እንደማውቀው ከሆነ ኅሊናዬ አይወቅሰኝም፤ ይህም እኔ ንጹሕ መሆኔን አያስረዳም፤ ነገር ግን በእኔ ላይ የሚፈርድ ጌታ ብቻ ነው። ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል። ወንድሞች ሆይ! እናንተን ለመጥቀም ብዬ በዚህ ጉዳይ እኔንና አጵሎስን እንደ ምሳሌ አድርጌ ተናገርኩ፤ ይህንንም ያደረግኹት “ከተጻፈው አትለፍ” የሚለውን ምክር ትርጒሙን ከእኛ እንድትማሩ ብዬ ነው፤ ስለዚህ በአንድ ሰው መመካት ሌላውን ሰው ግን መናቅ አይገባችሁም። አንተ ከሌሎች በምን ትበልጣለህ? ከሌላ ያልተቀበልከውስ ነገር ምን አለ? ታዲያ፥ ሁሉን ነገር የተቀበልከው ከሌላ ከሆነ እንዳልተቀበለ ሰው ስለምን ትመካለህ? አሁንማ የሚያስፈልጋችሁን ነገር ሁሉ አግኝታችኋል፤ አሁንማ ሀብታሞች ሆናችኋል፤ ከእኛም ተለይታችሁ ነግሣችኋል፤ በእርግጥ ብትነግሡማ ኖሮ፥ እኛም ከእናንተ ጋር አብረን ስለምንነግሥ መንገሣችሁ መልካም በሆነ ነበር፤ እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት ተፈርዶባቸው ወደሚገደሉበት ቦታ ከሚወሰዱት ሰዎች መካከል የመጨረሻዎቹ ያደረገን ይመስለኛል፤ ከዚህም የተነሣ በዓለም ሁሉ በመላእክትም ሆነ በሰዎች ፊት እንደ ትርኢት ሆነን እንታያለን፤ እኛ ስለ ክርስቶስ ብለን ሞኞች ሆነናል፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ጥበበኞች ሆናችኋል፤ እንዲሁም እኛ ደካሞች ሆነናል፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ሆናችኋል፤ እናንተ የተከበራችሁ ሆናችኋል፤ እኛ ግን የተዋረድን ሆነናል። አሁንም ቢሆን እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፤ እንጠማለን፤ እንራቈታለን፤ እንደበደባለን፤ መጠለያ በማጣት እንንከራተታለን። በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲረግሙን እንመርቃለን፤ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፤ ሲሰድቡንና ስማችንን ሲያጠፉ በትሕትና እንመልስላቸዋለን፤ እስከ አሁን ድረስ የዚህ ዓለም ውዳቂና የምድር ጥራጊ ጒድፍ ሆነናል።
1 ቆሮንቶስ 4:1-13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እኛ የክርስቶስ አገልጋዮችና የእግዚአብሔር የምሥጢሩ መጋቢዎች እንደ ሆን ሰው ስለ እኛ እንዲህ ያስብ። እንግዲህ በዚህ ከመጋቢዎች እያንዳንዱ ቸርና ታማኝ ሆኖ እንዲገኝ ይፈለጋል። ለእኔስ በእናንተ ዘንድ መመስገን ውርደት ነው፤ ጻድቅ ብትሉኝ፥ በመዋቲ ሰው ዘንድም ቸር ብላችሁ ብታከብሩኝ እኔ ለራሴ አልፈርድም። የሚያጠራጥረኝና ትዝ የሚለኝ ነገር የለም፤ በዚህም ራሴን አላመጻድቅም፤ እግዚአብሔር ይመረምረኛልና። ጊዜው ሳይደርስ ዛሬ ለምን ትመረምራላቸሁ? በጨለማ ውስጥ የተሰወረውንም የሚያበራ፥ የልብን አሳብም የሚገልጥ ጌታችን ይመጣል፤ ያንጊዜ ሁሉም ዋጋውን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል። ወንድሞቻችን ሆይ! እኔም፥ አጵሎስም ብንሆን መከራ የተቀበልነው ስለ እናንተ ነው፤ እናንተ እንድትማሩ፥ ከመጻሕፍት ቃልም ወጥታችሁ በወንድሞቻችሁ ላይ እንዳትታበዩ ነው። ማን ይመረምርሃል? የምትታበይስ በምንድን ነው? ከሌላ ያላገኘኸው አለህን? ያለህንም ከሌላ ካገኘህ እንዳላገኘ ለምን ትኮራለህ? እናንተ አሁን ጠግባችኋል፤ በልጽጋችኋልም፤ ያለእኛም ፈጽማችሁ ነግሣችኋል፤ እኛም ከእናንተ ጋር እንድንነግሥ ብትነግሡ አግባብ በሆነ ነበር። እኔስ ለሞት ዝግጁዎች እንደ መሆናችን እኛን ሐዋርያቱን እግዚአብሔር የኋለኞች ያደረገን ይመስለኛል፤ እኛ ለሰዎችም፥ ለአለቆችም፥ ለዓለምም መዘባበቻ ሆነናልና። እኛስ ስለ ክርስቶስ ብለን አላዋቂዎች ነን፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ጠቢባን ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ናችሁ፤ እናንተ ክቡራን ናችሁ፤ እኛ ግን የተዋረድን ነን። እኛ እስከዚች ቀን ድረስ እንራባለን፤ እንጠማለን፤ እንራቈታለን፤ እንሰደዳለን፤ ማረፊያም የለንም፤ እንደበደባለንም። በእጃችን ሥራ እያገለገልን እንደክማለን፤ ይረግሙናል፤ እኛ ግን እንመርቃቸዋለን፤ ያሳድዱናል፤ እኛ ግን እንጸልይላቸዋለን፤ እንታገሣቸዋለንም። ይሰድቡናል፥ እንማልዳቸዋለን፤ በዓለም እንደ ጊጤ ሆን፤ በሁሉም ዘንድ የተናቅን ሆን።
1 ቆሮንቶስ 4:1-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እንግዲህ ሰው ሁሉ እኛን እንደ ክርስቶስ አገልጋዮችና እንደ እግዚአብሔር ምስጢር ባለዐደራዎች ሊቈጥረን ይገባል። ባለዐደራዎችም ታማኝ ሆነው መገኘት አለባቸው። በእናንተም ሆነ በሰዎች የፍርድ ሸንጎ ቢፈረድብኝ እኔ በበኩሌ ግድ የለኝም፤ እኔ እንኳ በራሴ ላይ አልፈርድም። ኅሊናዬ ንጹሕ ነው፤ ይህ ግን ጥፋት አልባ መሆኔን አያረጋግጥም፤ በእኔ ላይ የሚፈርድ ጌታ ነው። ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ በምንም ነገር አትፍረዱ፤ ጌታ እስኪመጣ ጠብቁ። እርሱ በጨለማ ውስጥ የተሰወረውን ወደ ብርሃን ያመጣዋል፤ በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውንም ሐሳብ ይገልጠዋል። በዚያ ጊዜ እያንዳንዱ ሰው የሚገባውን ምስጋና ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል። እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ለእናንተ ጥቅም ብዬ በዚህ ጕዳይ እኔን ራሴንና አጵሎስን ምሳሌ አድርጌ አቅርቤላችኋለሁ፤ ይህንም ያደረግሁት፣ “ከተጻፈው አትለፍ” የሚለውን ከእኛ እንድትማሩ ነው። ስለዚህ አንዱን ሰው ከሌላው አብልጣችሁ አትመኩበት። ለመሆኑ፣ አንተን ከሌላው እንድትበልጥ ያደረገህ ማን ነው? ያልተቀበልኸው የራስህ የሆነ ነገር ምን አለ? ከተቀበልህ ታዲያ፣ እንዳልተቀበልህ ለምን ትመካለህ? አሁንስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝታችኋል! ሀብታምም ሆናችኋል! ከእኛም ተለይታችሁ ነግሣችኋል! በርግጥ ብትነግሡማ እኛም ከእናንተ ጋራ በነገሥን ነበር፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን፣ ሞት እንደ ተፈረደባቸው ሰዎች ከሰው ሁሉ መጨረሻ ያሰለፈን ይመስለኛል፤ ለዓለም ሁሉ፣ ለመላእክትም ለሰዎችም ትርኢት ሆነናል። እኛ ስለ ክርስቶስ ብለን ሞኞች ነን፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ጥበበኞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ናችሁ፤ እናንተ የተከበራችሁ ናችሁ፤ እኛ ግን የተዋረድን ነን። እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፤ እንጠማለን፤ እንራቈታለን፤ እንደበደባለን፤ ያለ መጠለያ እንንከራተታለን፤ በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲረግሙን እንመርቃለን፤ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፤ ስማችንን ሲያጠፉ መልካም እንመልሳለን፤ እስከ አሁንም ድረስ የዓለም ጕድፍ፣ የምድር ጥራጊ ሆነናል።
1 ቆሮንቶስ 4:1-13 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እንዲሁ ሰው እኛን እንደ ክርስቶስ ሎሌዎችና እንደ እግዚአብሔር ምሥጢር መጋቢዎች ይቍጠረን። እንደዚህም ሲሆን፥ በመጋቢዎች ዘንድ የታመነ ሆኖ መገኘት ይፈለጋል። ነገር ግን በእናንተ ዘንድ ወይም በሌላ ሰው ዘንድ ብፈረድ ለእኔ ምንም አይደለም፤ እኔም በራሴ እንኳ አልፈርድም፤ በራሴ ላይ ምንም አላውቅምና፥ ነገር ግን በዚህ አልጸድቅም፤ እኔን የሚፈርድ ግን ጌታ ነው። ስለዚህም በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል። ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አንዱ በአንዱ ላይ አንዳችሁም እንዳይታበዩ፦ ከተጻፈው አትለፍ የሚለውን በእኛ ትማሩ ዘንድ፥ ይህን በእናንተ ምክንያት ስለ ራሴና ስለ አጵሎስ እንደ ምሳሌ ተናገርሁ። አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልህ ከሆንህ ግን እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድር ነው? አሁን ጠግባችኋል፤ አሁንስ ባለ ጠጎች ሆናችኋል፤ ያለ እኛ ነግሣችኋል፤ እኛ ደግሞ ከእናንተ ጋር እንድንነግሥ ብትነግሡ መልካም ይሆን ነበር። ለዓለም ለመላእክትም ለሰዎችም መጫወቻ ሆነናልና፤ እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት እንደ ተፈረደባቸው ሰዎች ከሁሉ ይልቅ የኋለኞች እንዳደረገን ይመስለኛልና። እኛ ስለ ክርስቶስ ሞኞች ነን እናንተ ግን በክርስቶስ ልባሞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን እናንተ ግን ኃይለኞች ናችሁ፤ እናንተ የከበራችሁ ናችሁ እኛ ግን የተዋረድን ነን። እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፥ እንጠማለን፥ እንራቆታለን፥ እንጐሰማለን፥ እንንከራተታለን፥ በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲሰድቡን እንመርቃለን፥ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፥ ክፉ ሲናገሩን እንማልዳለን፤ እስከ አሁን ድረስ የዓለም ጥራጊ የሁሉም ጉድፍ ሆነናል።
1 ቆሮንቶስ 4:1-13 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እንግዲህ ሰው ሁሉ እኛን የክርስቶስ አገልጋዮች እንደ ሆንን የእግዚአብሔርንም ምሥጢር የመግለጥ ኀላፊነት የተሰጠን ባለ ዐደራዎች እንደ ሆንን አድርጎ ሊቈጥረን ይገባል። ባለ ዐደራዎችም ታማኞች ሆነው መገኘት አለባቸው። ስለ እኔ የሆነ እንደ ሆነ እናንተም ብትፈርዱብኝ ወይም ሌላ ሰው ቢፈርድብኝ ምንም ግድ የለኝም፤ በእውነቱ እኔ በራሴ ላይ እንኳ መፍረድ አልችልም። እኔ እንደማውቀው ከሆነ ኅሊናዬ አይወቅሰኝም፤ ይህም እኔ ንጹሕ መሆኔን አያስረዳም፤ ነገር ግን በእኔ ላይ የሚፈርድ ጌታ ብቻ ነው። ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል። ወንድሞች ሆይ! እናንተን ለመጥቀም ብዬ በዚህ ጉዳይ እኔንና አጵሎስን እንደ ምሳሌ አድርጌ ተናገርኩ፤ ይህንንም ያደረግኹት “ከተጻፈው አትለፍ” የሚለውን ምክር ትርጒሙን ከእኛ እንድትማሩ ብዬ ነው፤ ስለዚህ በአንድ ሰው መመካት ሌላውን ሰው ግን መናቅ አይገባችሁም። አንተ ከሌሎች በምን ትበልጣለህ? ከሌላ ያልተቀበልከውስ ነገር ምን አለ? ታዲያ፥ ሁሉን ነገር የተቀበልከው ከሌላ ከሆነ እንዳልተቀበለ ሰው ስለምን ትመካለህ? አሁንማ የሚያስፈልጋችሁን ነገር ሁሉ አግኝታችኋል፤ አሁንማ ሀብታሞች ሆናችኋል፤ ከእኛም ተለይታችሁ ነግሣችኋል፤ በእርግጥ ብትነግሡማ ኖሮ፥ እኛም ከእናንተ ጋር አብረን ስለምንነግሥ መንገሣችሁ መልካም በሆነ ነበር፤ እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት ተፈርዶባቸው ወደሚገደሉበት ቦታ ከሚወሰዱት ሰዎች መካከል የመጨረሻዎቹ ያደረገን ይመስለኛል፤ ከዚህም የተነሣ በዓለም ሁሉ በመላእክትም ሆነ በሰዎች ፊት እንደ ትርኢት ሆነን እንታያለን፤ እኛ ስለ ክርስቶስ ብለን ሞኞች ሆነናል፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ጥበበኞች ሆናችኋል፤ እንዲሁም እኛ ደካሞች ሆነናል፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ሆናችኋል፤ እናንተ የተከበራችሁ ሆናችኋል፤ እኛ ግን የተዋረድን ሆነናል። አሁንም ቢሆን እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፤ እንጠማለን፤ እንራቈታለን፤ እንደበደባለን፤ መጠለያ በማጣት እንንከራተታለን። በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲረግሙን እንመርቃለን፤ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፤ ሲሰድቡንና ስማችንን ሲያጠፉ በትሕትና እንመልስላቸዋለን፤ እስከ አሁን ድረስ የዚህ ዓለም ውዳቂና የምድር ጥራጊ ጒድፍ ሆነናል።
1 ቆሮንቶስ 4:1-13 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
እንግዲህ ሰው እኛን እንደ ክርስቶስ አገልጋዮችና እንደ እግዚአብሔር ምሥጢራት መጋቢዎች ይቁጠረን። ከዚህም በላይ፥ በመጋቢዎች ዘንድ የታመነ ሆኖ መገኘት ያሻል። ነገር ግን በእናንተ ዘንድ ወይም በማንም ሰው ዘንድ ቢፈረድብኝ ለእኔ ምንም አይደለም፤ እኔም በራሴ እንኳ አልፈርድም፤ በራሴ ላይ ከኅሊናዬ ምንም የለም፤ ነገር ግን በዚህ አልጸድቅም፤ በእኔ ላይ የሚፈርድ ግን ጌታ ነው። ስለዚህም፥ በጨለማ የተሰወረውን ወደ ብርሃን የሚያወጣ ደግሞም የልብን ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ፥ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም እያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል። ወንድሞች ሆይ! ስለ አንዱ በሌላው ላይ አንዳችሁም እንዳትታበዩ “ከተጻፈው አትለፍ፤” የሚለውን በእኛ እንድትማሩ፥ በዚህ ስለ እናንተ ስል ራሴንና አጵሎስን እንደ ምሳሌ ተናገርሁ። አንተን እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልከውስ ምን አለህ? እንግዲህ የተቀበልክ ከሆንክ፥ እንዳልተቀበልክ የምትመካው ስለ ምንድነው? አሁንማ ሞልቶላችኋል! አሁንማ ሀብታሞች ሆናችኋል! ያለ እኛ ነግሣችኋል! እኛም ከእናንተ ጋር እንድንነግሥ፥ በእርግጥ ብትነግሡ ኖሮ፥ መልካም በሆነ! እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት እንደ ተፈረደባቸው ሰዎች ከሁሉ ይልቅ የኋለኞች እንዳደረገን ይመስለኛል፤ ምክንያቱም ለዓለም ለመላእክትም ለሰዎችም ትንግርት ሆነናል። እኛ ስለ ክርስቶስ ሞኞች ነን፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ልባሞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ናችሁ፤ እናንተ የተከበራችሁ ናችሁ፤ እኛ ግን የተዋረድን ነን። እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፥ እንጠማለንም፤ እንራቆታለን፥ እንጐሰማለንም፥ እንዲሁም እንንከራተታለን፤ በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲረግሙን እንመርቃለን፤ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፤ ክፉ ሲናገሩን በትሕትና እንመልስላቸዋለን፤ እስከ አሁን ድረስ የዚህ ዓለም ጥራጊ የሁሉም ጉድፍ ሆነናል።