እኛ የክርስቶስ አገልጋዮችና የእግዚአብሔር የምሥጢሩ መጋቢዎች እንደ ሆን ሰው ስለ እኛ እንዲህ ያስብ። እንግዲህ በዚህ ከመጋቢዎች እያንዳንዱ ቸርና ታማኝ ሆኖ እንዲገኝ ይፈለጋል። ለእኔስ በእናንተ ዘንድ መመስገን ውርደት ነው፤ ጻድቅ ብትሉኝ፥ በመዋቲ ሰው ዘንድም ቸር ብላችሁ ብታከብሩኝ እኔ ለራሴ አልፈርድም። የሚያጠራጥረኝና ትዝ የሚለኝ ነገር የለም፤ በዚህም ራሴን አላመጻድቅም፤ እግዚአብሔር ይመረምረኛልና። ጊዜው ሳይደርስ ዛሬ ለምን ትመረምራላቸሁ? በጨለማ ውስጥ የተሰወረውንም የሚያበራ፥ የልብን አሳብም የሚገልጥ ጌታችን ይመጣል፤ ያንጊዜ ሁሉም ዋጋውን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል። ወንድሞቻችን ሆይ! እኔም፥ አጵሎስም ብንሆን መከራ የተቀበልነው ስለ እናንተ ነው፤ እናንተ እንድትማሩ፥ ከመጻሕፍት ቃልም ወጥታችሁ በወንድሞቻችሁ ላይ እንዳትታበዩ ነው። ማን ይመረምርሃል? የምትታበይስ በምንድን ነው? ከሌላ ያላገኘኸው አለህን? ያለህንም ከሌላ ካገኘህ እንዳላገኘ ለምን ትኮራለህ? እናንተ አሁን ጠግባችኋል፤ በልጽጋችኋልም፤ ያለእኛም ፈጽማችሁ ነግሣችኋል፤ እኛም ከእናንተ ጋር እንድንነግሥ ብትነግሡ አግባብ በሆነ ነበር። እኔስ ለሞት ዝግጁዎች እንደ መሆናችን እኛን ሐዋርያቱን እግዚአብሔር የኋለኞች ያደረገን ይመስለኛል፤ እኛ ለሰዎችም፥ ለአለቆችም፥ ለዓለምም መዘባበቻ ሆነናልና። እኛስ ስለ ክርስቶስ ብለን አላዋቂዎች ነን፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ጠቢባን ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ናችሁ፤ እናንተ ክቡራን ናችሁ፤ እኛ ግን የተዋረድን ነን። እኛ እስከዚች ቀን ድረስ እንራባለን፤ እንጠማለን፤ እንራቈታለን፤ እንሰደዳለን፤ ማረፊያም የለንም፤ እንደበደባለንም። በእጃችን ሥራ እያገለገልን እንደክማለን፤ ይረግሙናል፤ እኛ ግን እንመርቃቸዋለን፤ ያሳድዱናል፤ እኛ ግን እንጸልይላቸዋለን፤ እንታገሣቸዋለንም። ይሰድቡናል፥ እንማልዳቸዋለን፤ በዓለም እንደ ጊጤ ሆን፤ በሁሉም ዘንድ የተናቅን ሆን።
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 4 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 4
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 4:1-13
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች