መጽሐፈ መሳፍንት 15:13-20

መጽሐፈ መሳፍንት 15:13-20 አማ54

እነርሱም፦ አስረን በእጃቸው አሳልፈን እንሰጥሃለን እንጂ አንገድልህም ብለው ተናገሩት። በሁለትም አዲስ ገመድ አስረው ከዓለቱ ውስጥ አወጡት። ወደ ሌሒ በመጣ ጊዜም ፍልስጥኤማውያን እልል እያሉ ተገናኙት። የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ወረደበት፥ ክንዱም የታሰረበት ገመድ በእሳት እንደ ተበላ እንደ ተልባ እግር ፈትል ሆነ፥ ማሰሪያዎቹም ከእጁ ወደቁ። አዲስም የአህያ መንጋጋ አገኘ፥ እጁንም ዘርግቶ ወሰደው፥ በእርሱም አንድ ሺህ ሰው ገደለ። ሶምሶንም፦ በአህያ መንጋጋ ክምር በክምር ላይ አድርጌአቸዋለሁ፥ በአህያ መንጋጋ አንድ ሺህ ሰው ገድያለሁ አለ። መናገሩንም በፈጸመ ጊዜ መንጋጋውን ከእጁ ጣለ፥ የዚያንም ስፍራ ስም ራማትሌሒ ብሎ ጠራው። እርሱም እጅግ ተጠምቶ ነበርና፦ አንተ ይህችን ታላቅ ማዳን በባሪያህ እጅ ሰጥተሃል፥ አሁንም በጥም እሞታለሁ፥ ባልተገረዙትም እጅ እወድቃለሁ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። እግዚአብሔርም በሌሒ ያለውን አዘቅት ሰነጠቀ፥ ከእርሱም ውኃ ወጣ፥ እርሱም ጠጣ፥ ነፍሱም ተመለሰች፥ ተጠናከረም። ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም ዓይንሀቆሬ ብሎ ጠራው፥ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በሌሒ አለ። በፍልስጥኤማውያንም ዘመን በእስራኤል ላይ ሀያ ዓመት ፈረደ።