መሳፍንት 15:13-20

መሳፍንት 15:13-20 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እነርሱም፣ “አስረን ብቻ ለእነርሱ አሳልፈን እንሰጥሃለን እንጂ ራሳችን አንገድልህም” አሉት፤ ከዚያ በሁለት አዳዲስ ገመድ አስረው ከዐለቱ ዋሻ አወጡት። ሳምሶን ሌሒ እንደ ደረሰም ፍልስጥኤማውያን እየጮኹ ወደ እርሱ መጡ፤ በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በሳምሶን ላይ በኀይል ወረደበት። እጆቹ የታሰሩበትም ገመድ እሳት ውስጥ እንደ ገባ የተልባ እግር ፈትል ሆኖ ከእጆቹ ላይ ወደቀ። ከዚያም በቅርቡ የሞተ የአንድ የአህያ መንጋጋ አይቶ ከመሬት አነሣ፤ በዚያም አንድ ሺሕ ሰው ገደለ። ሳምሶንም፣ “በአንድ የአህያ መንጋጋ፣ ሺሕ ሰው ዘራሪ፤ በአንድ የአህያ መንጋጋ፣ ሺሕ ሬሳ አነባባሪ” ብሎ ፎከረ። ይህን ተናግሮ እንዳበቃ የአህያውን መንጋጋ ከእጁ ወዲያ ወረወረው፤ የዚያም ቦታ ስም ራማት ሌሒ ተብሎ ተጠራ። እጅግ ተጠምቶ ስለ ነበር፤ “እነሆ፤ ለአገልጋይህ ይህን ታላቅ ድል አጐናጽፈሃል፤ ታዲያ አሁን በውሃ ጥም ልሙት? እንዴትስ በእነዚህ ባልተገረዙ ፍልስጥኤማውያን እጅ ልውደቅ?” በማለት ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። እግዚአብሔርም በሌሒ ዐለት ሰነጠቀለት፤ ከዚያም ውሃ ወጣ፤ ሳምሶንም ያን ሲጠጣ በረታ፤ መንፈሱም ታደሰ። ስለዚህ ያ ምንጭ ዓይንሀቆሬ ተባለ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያው በሌሒ ይገኛል። ሳምሶንም በፍልስጥኤማውያን ዘመን በእስራኤል ላይ ለሃያ ዓመት ፈራጅ ሆነ።

መሳፍንት 15:13-20 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እነ​ር​ሱም፥ “በገ​መድ አስ​ረን በእ​ጃ​ቸው አሳ​ል​ፈን እን​ሰ​ጥ​ሃ​ለን እንጂ አን​ገ​ድ​ል​ህም” ብለው ማሉ​ለት። በሁ​ለ​ትም አዲስ ገመድ አስ​ረው ከዓ​ለቱ ውስጥ አወ​ጡት። የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት ወደ ተባለ ቦታም ደረሰ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ደን​ፍ​ተው ተቀ​በ​ሉት፤ ወደ እር​ሱም ሮጡ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ አደረ፤ በክ​ን​ዱም ያሉ እነ​ዚያ ገመ​ዶች በእ​ሳት ላይ እንደ ተጣለ ገለባ ሆኑ፤ ማሰ​ሪ​ያ​ውም ከክ​ንዱ ተፈታ፤ የወ​ደቀ የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ን​ት​ንም በመ​ን​ገድ አገኘ። እጁ​ንም ዘር​ግቶ ወሰ​ደው፤ በእ​ር​ሱም አንድ ሺህ ሰው ገደለ። ሶም​ሶ​ንም፥ “በአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት ክምር በክ​ምር ላይ አድ​ር​ጌ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት አንድ ሺህ ሰው ገድ​ያ​ለ​ሁና” አለ። መና​ገ​ሩ​ንም በፈ​ጸመ ጊዜ መን​ጋ​ጋ​ውን ከእጁ ጣለ፤ የዚ​ያ​ንም ስፍራ ስም “ቀትለ አጽመ መን​ሰክ” ብሎ ጠራው። እር​ሱም እጅግ ተጠ​ምቶ ነበ​ርና፥ “አንተ ይህ​ችን ታላቅ ማዳን በባ​ሪ​ያህ እጅ ሰጥ​ተ​ሃል፤ አሁ​ንም በጥም እሞ​ታ​ለሁ፤ ባል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትም እጅ እወ​ድ​ቃ​ለሁ” ብሎ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የዚ​ያ​ችን የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት ስን​ጥ​ቃት ከፈተ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ውኃ ወጣ፤ እር​ሱም ጠጣ፤ ነፍ​ሱም ተመ​ለ​ሰች፤ ከውኃ ጥሙም ዐረፈ። ስለ​ዚ​ህም የዚያ ቦታ ስም እስከ ዛሬ ድረስ “ነቅዐ አጽመ መን​ሰክ” ተብሎ ተጠራ። በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ዘመን እስ​ራ​ኤ​ልን ሃያ ዓመት ገዛ​ቸው።

መሳፍንት 15:13-20 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እነርሱም፣ “አስረን ብቻ ለእነርሱ አሳልፈን እንሰጥሃለን እንጂ ራሳችን አንገድልህም” አሉት፤ ከዚያ በሁለት አዳዲስ ገመድ አስረው ከዐለቱ ዋሻ አወጡት። ሳምሶን ሌሒ እንደ ደረሰም ፍልስጥኤማውያን እየጮኹ ወደ እርሱ መጡ፤ በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በሳምሶን ላይ በኀይል ወረደበት። እጆቹ የታሰሩበትም ገመድ እሳት ውስጥ እንደ ገባ የተልባ እግር ፈትል ሆኖ ከእጆቹ ላይ ወደቀ። ከዚያም በቅርቡ የሞተ የአንድ የአህያ መንጋጋ አይቶ ከመሬት አነሣ፤ በዚያም አንድ ሺሕ ሰው ገደለ። ሳምሶንም፣ “በአንድ የአህያ መንጋጋ፣ ሺሕ ሰው ዘራሪ፤ በአንድ የአህያ መንጋጋ፣ ሺሕ ሬሳ አነባባሪ” ብሎ ፎከረ። ይህን ተናግሮ እንዳበቃ የአህያውን መንጋጋ ከእጁ ወዲያ ወረወረው፤ የዚያም ቦታ ስም ራማት ሌሒ ተብሎ ተጠራ። እጅግ ተጠምቶ ስለ ነበር፤ “እነሆ፤ ለአገልጋይህ ይህን ታላቅ ድል አጐናጽፈሃል፤ ታዲያ አሁን በውሃ ጥም ልሙት? እንዴትስ በእነዚህ ባልተገረዙ ፍልስጥኤማውያን እጅ ልውደቅ?” በማለት ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። እግዚአብሔርም በሌሒ ዐለት ሰነጠቀለት፤ ከዚያም ውሃ ወጣ፤ ሳምሶንም ያን ሲጠጣ በረታ፤ መንፈሱም ታደሰ። ስለዚህ ያ ምንጭ ዓይንሀቆሬ ተባለ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያው በሌሒ ይገኛል። ሳምሶንም በፍልስጥኤማውያን ዘመን በእስራኤል ላይ ለሃያ ዓመት ፈራጅ ሆነ።

መሳፍንት 15:13-20 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እነርሱም፦ አስረን በእጃቸው አሳልፈን እንሰጥሃለን እንጂ አንገድልህም ብለው ተናገሩት። በሁለትም አዲስ ገመድ አስረው ከዓለቱ ውስጥ አወጡት። ወደ ሌሒ በመጣ ጊዜም ፍልስጥኤማውያን እልል እያሉ ተገናኙት። የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ወረደበት፥ ክንዱም የታሰረበት ገመድ በእሳት እንደ ተበላ እንደ ተልባ እግር ፈትል ሆነ፥ ማሰሪያዎቹም ከእጁ ወደቁ። አዲስም የአህያ መንጋጋ አገኘ፥ እጁንም ዘርግቶ ወሰደው፥ በእርሱም አንድ ሺህ ሰው ገደለ። ሶምሶንም፦ በአህያ መንጋጋ ክምር በክምር ላይ አድርጌአቸዋለሁ፥ በአህያ መንጋጋ አንድ ሺህ ሰው ገድያለሁ አለ። መናገሩንም በፈጸመ ጊዜ መንጋጋውን ከእጁ ጣለ፥ የዚያንም ስፍራ ስም ራማትሌሒ ብሎ ጠራው። እርሱም እጅግ ተጠምቶ ነበርና፦ አንተ ይህችን ታላቅ ማዳን በባሪያህ እጅ ሰጥተሃል፥ አሁንም በጥም እሞታለሁ፥ ባልተገረዙትም እጅ እወድቃለሁ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። እግዚአብሔርም በሌሒ ያለውን አዘቅት ሰነጠቀ፥ ከእርሱም ውኃ ወጣ፥ እርሱም ጠጣ፥ ነፍሱም ተመለሰች፥ ተጠናከረም። ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም ዓይንሀቆሬ ብሎ ጠራው፥ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በሌሒ አለ። በፍልስጥኤማውያንም ዘመን በእስራኤል ላይ ሀያ ዓመት ፈረደ።

መሳፍንት 15:13-20 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እነርሱም “መልካም ነው፤ አንተን በገመድ አስረን ለእነርሱ አሳልፈን እንሰጥሃለን እንጂ እኛስ አንገድልህም” ሲሉ መለሱለት። ከዚህም በኋላ በሁለት አዳዲስ ገመዶች አሰሩትና ከዋሻው አውጥተው ወሰዱት። ሶምሶንም ወደ ሌሒ በመጣ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እየደነፉ መጡበት፤ የእግዚአብሔር መንፈስ አበረታው፤ ክንዱ የታሰሩበት ገመዶች እሳት እንደ ነካቸው የሐር ፈትል ከእጁ ላይ ቀልጠው ወደቁ። ከዚህ በኋላ በቅርብ ጊዜ የሞተ የአንድ አህያ መንጋጋ አገኘ፤ ጐንበስ ብሎ አንሥቶም አንድ ሺህ ሰው ገደለበት። ሶምሶንም፥ “በአህያ መንጋጋ አንድ ሺህ ሰው ገደልኩ፤ በዚህም የአህያ መንጋጋ ሬሳውን በሬሳ ላይ ከመርሁ” አለ። ከዚያም በኋላ ይዞት የነበረውን መንጋጋ ወረወረው፤ ይህም የተፈጸመበት ያ ስፍራ “ራማት ሌሒ” ተብሎ ተጠራ። ከዚህ በኋላ ሶምሶን በጣም ተጠማ፤ ወደ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ጮኸ፤ “ይህን ትልቅ ድል ለአገልጋይህ ሰጥተኸኛል፤ ታዲያ፥ እኔ አሁን በውሃ ጥም ልሙትን? ባልተገረዙ ሰዎች እጅም ልውደቅን?” እግዚአብሔር በሌሂ ያለው ጐድጓዳ ቦታ ከፈተለት፤ ከእርሱም ውሃ ወጣ፤ በጠጣም ጊዜ መንፈሱ ተመልሶለት ተጠናከረ፤ ስለዚህም ያ ቦታ “ዐይን ሃቆሬ” የተባለ። እርሱም እስከ ዛሬ ድረስ በሌሂ ይገኛል። ፍልስጥኤማውያን በሀገሩ ላይ ገዢዎች በነበሩበት ዘመን ሶምሶን እስራኤልን ለኻያ ዓመት ሙሉ መራ።

መሳፍንት 15:13-20 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እነርሱም፥ “አስረን ብቻ ለእነርሱ አሳልፈን እንሰጥሃለን እንጂ ራሳችን አንገድልህም” አሉት፤ ከዚያ በሁለት አዳዲስ ገመድ አስረው ከዐለቱ ዋሻ አወጡት። ሳምሶን ሌሒ እንደደረሰም ፍልስጥኤማውያን እየጮኹ ወደ እርሱ መጡ፤ በዚህ ጊዜ የጌታ መንፈስ በሳምሶን ላይ በኃይል ወረደበት። እጆቹ የታሰሩበትም ገመድ እሳት ውስጥ እንደ ገባ የተልባ እግር ፈትል ሆኖ ከእጆቹ ላይ ወደቀ። ከዚያም በቅርቡ የሞተ የአንድ የአህያ መንጋጋ አይቶ ከመሬት አነሣ፤ በዚያም አንድ ሺህ ሰው ገደለ። ሳምሶንም፥ “በአንድ የአህያ መንጋጋ፥ ሺህ ሰው ዘራሪ፤ በአንድ የአህያ መንጋጋ፥ ሺህ ሬሳ አነባባሪ!” ብሎ ፎከረ። ይህን ተናግሮ እንዳበቃ የአህያውን መንጋጋ ከእጁ ወዲያ ወረወረው፤ የዚያም ቦታ ስም ራማት ሌሒሰ ተብሎ ተጠራ። እጅግ ተጠምቶ ስለ ነበር፤ “እነሆ፤ ለአገልጋይህ ይህን ታላቅ ድል አጐናጽፈሃል፤ ታዲያ አሁን በውሃ ጥም ልሙት? እንዴትስ በእነዚህ ባልተገረዙ ፍልስጥኤማውያን እጅ ልውደቅ?” በማለት ወደ ጌታ ጮኸ። እግዚአብሔርም በሌሒ ዐለት ሰነጠቀለት፤ ከዚያም ውኃ ወጣ፤ ሳምሶንም ያን ሲጠጣ በረታ፤ መንፈሱም ታደሰ። ስለዚህ ያ ምንጭ ዓይንሀቆሬሸ ተባለ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያው በሌሒ ይገኛል። ሳምሶንም በፍልስጥኤማውያን ዘመን በእስራኤል ላይ ለሃያ ዓመት ፈራጅቀ ሆነ።