ከመርከብ የወጡት የኖኅ ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ሴም፥ ካም፥ ያፌት፤ ካምም የከነዓን አባት ነው። የኖኅ ልጆች እነዚህ ሦስቱ ናቸው ከእነርሱም ምድር ሁሉ ተሞካች። ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፥ ወይንም ተከለ። ከወይን ጠጁም ጠጣና ስከረ በድንኳኑም ውስጥ ዕርቁቱን ሆነ። የከነዓን አባት ካምም የአባቱን ዕራቁትነት አየ፥ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። ሴምና ያፌትም ሸማወስደው በጫንቃአው ላይ አደረጉ፥ የኋሊትም ሄደው የአባታቸወን ዕራቁትነት አለበሱ፥ ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበረ፥ የአባታቸውንም ዕራቁትነት አላዩም። ኖኅም ከወይን ጠጅ ስካር ነቃ፥ ታናሹ ልጁ ያደረገበትንም አወቀ። እንዲህም አለ፥ ከነዓን ርጉም ይሁን ለወንድሞቹም የባሪያዎች ባሪያ ይሁን። እንዲህም አለ፤ የሴም አምላክ እግዚእብሔር ይባረን፥ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን። እግዚአብሔርም ያፌትን ያስፋ፥ በሴምም ድንኳን ይደር ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን። ኖኅም ከጥፋት ውኃ በኍላ ሦስት መቶ አምሳ ዓመት ኖረ። ኖኅም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አምሳ ዓመት ሆነ ሞተም።
ኦሪት ዘፍጥረት 9 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 9:18-29
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos