ከመርከቧ የወጡትም የኖኅ ልጆች ሴም፣ ካምና ያፌት ነበሩ፤ ካም የከነዓን አባት ነው። ሦስቱ የኖኅ ልጆች እነዚህ ሲሆኑ፣ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ የተገኙት ከእነዚሁ ነው። ኖኅ ገበሬ ነበረና ወይን ተከለ፤ ከወይኑም ጠጅ ጠጥቶ ሰከረና በድንኳኑ ውስጥ ዕርቃኑን ተኛ። የከነዓን አባት ካም የአባቱን ዕርቃነ ሥጋ አየ፤ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። ሴምና ያፌት ግን ልብስ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉና የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ እንዳያዩ ፊታቸውን አዙረው የኋሊት በመሄድ የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ ሸፈኑ። ኖኅ ከወይን ጠጁ ስካር ሲነቃ፣ ታናሽ ልጁ ያደረገበትን ዐወቀ፤ እንዲህም አለ፤ “ከነዓን የተረገመ ይሁን፤ ለወንድሞቹም፣ የባሪያ ባሪያ ይሁን።” ደግሞም፤ “የሴም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፤ ከነዓንም የሴም ባሪያ ይሁን። እግዚአብሔር የያፌትን ግዛት ያስፋ፤ ያፌት በሴም ድንኳኖች ይኑር፤ ከነዓንም የርሱ ባሪያ ይሁን” አለ። ኖኅ ከጥፋት ውሃ በኋላ 350 ዓመት ኖረ፤ ኖኅ በአጠቃላይ 950 ዓመት ኖሮ ሞተ።
ዘፍጥረት 9 ያንብቡ
ያዳምጡ ዘፍጥረት 9
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዘፍጥረት 9:18-29
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos