የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 9:18-29

ኦሪት ዘፍጥረት 9:18-29 አማ05

ከመርከቡ የወጡት የኖኅ ልጆች ሴም፥ ካምና ያፌት ናቸው፤ ካም የከነዓን አባት ነው፤ አሁን በምድር ላይ ተበትነው ያሉት ሰዎች ሁሉ የተገኙት ከእነዚህ ከሦስቱ የኖኅ ልጆች ነው። ኖኅ ገበሬ ነበረ፤ የወይን ተክልንም መትከል ጀመረ፤ ከዕለታት አንድ ቀን ኖኅ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሰከረ፤ ልብሱንም አውልቆ ራቊቱን በድንኳን ውስጥ ተኛ። የከነዓን አባት የሆነው ካም፥ አባቱ ኖኅ እራቁቱን እንደ ሆነ ባየ ጊዜ ወደ ውጪ ወጥቶ፥ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። ሴምና ያፌትም ልብስ በስተኋላቸው፥ በትከሻቸው ያዙ፤ ወደ ድንኳኑም የኋሊት ሄዱና የአባታቸውን ራቊትነት እንዳያዩ ፊታቸውን አዙረው ራቊትነቱን ሸፈኑ፤ የአባታቸውንም ራቊትነት ኣላዩም። ኖኅ ስካሩ አልፎለት ሲነቃ፥ ትንሹ ልጁ ያደረገበትን ዐወቀ፤ እንዲህም አለ፤ “ከነዓን የተረገመ ይሁን! ለወንድሞቹ የአገልጋዮች አገልጋይ ይሁን፤ እንደገናም እንዲህ አለ፤ የሴም አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን! ከነዓንም የሴም አገልጋይ ይሁን! እግዚአብሔር የያፌትን ምድር ያስፋ! የያፌት ዘሮች ከሴም ዘሮች ጋር አብረው ይኑሩ! ከነዓን የያፌት አገልጋይ ይሁን።” ከጥፋት ውሃ በኋላ ኖኅ 350 ዓመት ኖረ። ዕድሜውም 950 ዓመት ሲሆነው ሞተ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}