ኦሪት ዘፍጥረት 44:18-34

ኦሪት ዘፍጥረት 44:18-34 አማ54

ይሁዳም ወደ እርሱ ቀረበ እንዲህም አለ፦ ጌታዬ ሆይ እኔ ባርያን በጌታዬ ጆሮ አንዲት ቃልን እንድናገር እለምናለሁ እኔንም ባሪያህን አትቆጣኝ አንተ እንደ ፈርዖን ነህና። ጌታዬ ባሪያዎቹን፦ አባት አላችሁን ወይስ ወንድም? ብሎ ጠየቀ። እኛም ለጌታዬ እንዲህ አልነ፦ ሸማግሌ አባት አለን በሽምግልናው የወለደውም ታናሽ ብላቴና አለ ወንድሙም ሞተ ከእናቱም እርሱ ብቻውን ቀረ አባቱም ይወድደዋል። አንተም ለባሪያዎችህ፦ ወደ እኔ አምጡት እኔም አየዋለሁ አልህ። ጌታዬንም፦ ብላቴናው አባቱን መተው አይሆንለትም የተወው እንደ ሆነ አባቱ ይሞታልና አልነው። ባርያዎችህንም፦ ታናሽ ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ካልመጣ ዳግመኛ ፊቴን አታዮም አልኽን። ወደ ባርያህ ወደ አባታችን በተመለስን ጊዜም የጌታዮን ቃል ነገርነው። አባታችንም፦ ተመልሳችሁ ጥቂት እህል ሸምቱ ልን አለ። እኛም አልነው፦ እንሄድ ዘንድ አይሆንልንም ታናሹ ወንድማችን ከእኛ ጋር ይወርድ እንደ ሆነ እኝም እንወርዳለን ታናሹ ወንድማችን ከእኝ ጋር ከሌለ የዚያን ሰው ፊት ማየት አይቻለንምና ባሪያን አባቴም እንዲህ አለን፦ ሚስቴ ሁለት ወንዶች ልጆችን እንደ ወለደችልኝ እናንተ ታውቃላችሁ፤ አንዱም ከእኔ ወጣ፦ አውሬ በላው አላችሁኝ እስከ ዛሬም አላየሁትም፤ ይህንም ከእኔ ለይታችሁ ደግሞ ብትወስዱት ክፋም ቢያገኘው ሽበቴን በኅዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ። አሁንም እኔ ወደ አባቴ ወደ ባሪያህ ብሄድ ብላቴናውም ከእኛ ጋር ከሌለ ነፍሱ በብላቴናው ነፍስ ታስራለችና ብላቴናው ለእን ጋር እንደሌለ ባየ ጊዜ ይሞታል ባሪያዎህም የባሪያህን የአባታችንን ሽበት በኅዘን ወደ መቃብር ያወርዳሉ። እኔ ባሪያህ በአባቴ ዘንድ ስለ ብላቴናው እንዲህ ብዮ ተውሼአለሁና፦ እርሱንስ ወደ አንተ ባለመጣው በአባቴ ሀዘኔ በዘመናት ሁሉ ኃጢአተኛ እሆናለሁ። ስለዚህም እኔ ባሪያህ በጌታዬ ዘንድ ባሪያ ሆኜ በብላቴናው ፋንታ ልቀመጥ ብላቴናውም ከወንድሞቹ ጋር ይውጣ። አለዚያም ብላቴናው ከእኔ ጋር ከሌለ ወደ አባቴ እንዴት እወጣለሁ? አባቴን የሚያገኘውን መከራ እንዳላይ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}