የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 44

44
1ዮሴፍም የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘ፦ ዓይበታቸው የሚያነሣውን ያህል እህል ሙላላቸው የሁሉንም ብር በየዓይበታቸው አፍ ጨምረው፤ 2በታናሹም ዓይበት አፍ የብሩን ጽዋዬና የእህሉን ዋጋ ጨምራው። 3እርሱም ዮሴፍ እንዳለው አደረገ። ነገህ በሆነ ጊዜም ሰዎቹ አህዮቻቸውን ይዘው ይሄዱ ዘንድ ተሰናበቱ። 4ከከተማይቱም ወጥተው ገና ሳይርቁ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ አለ፦ ተነሥተህ ሰዎቹና ተከተላቸው በደረስህባቸውም ጊዜ እንዲህ በላቸው፦ በመልካሙ ፋንታ፥ 5ስለ ምን ክፋን መለሳችህ? ጌታዬ የሚጠጣበት ምሥጢርንም የሚያውቅበት ጽዋ አይደለምን? ባደረጋችሁች ነገር በደላችሁ። 6እርሱም ደርሰባቸው ይህንም ቃል ነገራቸው። 7እነርሱም አሉት፦ ጌታዬ እንደዚህ ያለው ቃል ለምን ይናገራል? ባሪያዎችህ ያለውን ቃል ለምን ይናገራል? ባሪያዎችህ ይህን ነገር የሚያደርጉ አይደሉም። 8እነሆ በዓይበታችን አፍ ያገኘነውን ብር ይዘን ከከነዓን አገር ወደ አንተ ተመልሰናል ከጌታህ ቤት ወርቅ ወይስ በር እንዴት እንሰርቃለን? 9ከባሪያዎችህ ጽዋው የተገኘበት እርሱ ይሙት እኛም ደግሞ ለጌታችን ባሪያዎች እንሁን። 10እርሱም አለ፦ አሁንም እንዲህ እንደ ነገራችሁ ይሁን ጽዋው የተገኘበት እርሱ ለእኔ ባሪያ ይሁነኝ እናንተም ንጽሐን ትሆናላችሁ፤ 11እየራሳቸውም ፈጥነው ዓይበታቸውን ወደ ምድር አወረዱ፥ እየራሳቸውም ዓይበታቸውን ፈቱ። 12እርሱም ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ በረበራቸው ጽዋውንም በብንያም ዓይበት ውስጥ አገኘው። 13ልብሳቸውንም ቀደዱ ዓይበታቸውንም በየአህዮቻቸው ጭነው ወደ ከተማይቱ ተመለሱ።
14ይሁዳም ከወንድሞቹ ጋር ወደ ዮሴፍ ገባ እርሱም ገና ከዚያው ነበረ፤ በፊቱም በምድር ላይ ወደቁ። 15ዮሴፍም ይህ ያደረጋችሁት ነገር ምንድር ነው? እንደ እኔ ያለ ሰው ምሥጢርን እንድያውቅ አታውቁምን? አላቸው። 16ይሁዳም አለ፦ ለጌታዬ ምን እንመልሳለን? ምንስ እንናገራለን? ወይስ በምን እንነጻለን? እግዚአብሔር የባሪያዎችህን ኃጢአት ገለጠ እነሆ እኝም ጽዋው ከእርሱ ዘንድ የተገኘበቱም ደግሞ ለጌታዬ ባሪያዎቹ ነን። 17እርሱም እላቸው፦ ይህን አደርግ ዘንድ አይሆንልኝም ጽዋው የተገኘበቱ ሰው እርሱ ባሪያ ይሁነኝ እናንተም ወደ አባታችሁ በደኅና ውጡ።
18ይሁዳም ወደ እርሱ ቀረበ እንዲህም አለ፦ ጌታዬ ሆይ እኔ ባርያን በጌታዬ ጆሮ አንዲት ቃልን እንድናገር እለምናለሁ እኔንም ባሪያህን አትቆጣኝ አንተ እንደ ፈርዖን ነህና። 19ጌታዬ ባሪያዎቹን፦ አባት አላችሁን ወይስ ወንድም? ብሎ ጠየቀ። 20እኛም ለጌታዬ እንዲህ አልነ፦ ሸማግሌ አባት አለን በሽምግልናው የወለደውም ታናሽ ብላቴና አለ ወንድሙም ሞተ ከእናቱም እርሱ ብቻውን ቀረ አባቱም ይወድደዋል። 21አንተም ለባሪያዎችህ፦ ወደ እኔ አምጡት እኔም አየዋለሁ አልህ። 22ጌታዬንም፦ ብላቴናው አባቱን መተው አይሆንለትም የተወው እንደ ሆነ አባቱ ይሞታልና አልነው። 23ባርያዎችህንም፦ ታናሽ ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ካልመጣ ዳግመኛ ፊቴን አታዮም አልኽን። 24ወደ ባርያህ ወደ አባታችን በተመለስን ጊዜም የጌታዮን ቃል ነገርነው። 25አባታችንም፦ ተመልሳችሁ ጥቂት እህል ሸምቱ ልን አለ። 26እኛም አልነው፦ እንሄድ ዘንድ አይሆንልንም ታናሹ ወንድማችን ከእኛ ጋር ይወርድ እንደ ሆነ እኝም እንወርዳለን ታናሹ ወንድማችን ከእኝ ጋር ከሌለ የዚያን ሰው ፊት ማየት አይቻለንምና ባሪያን አባቴም እንዲህ አለን፦ 27ሚስቴ ሁለት ወንዶች ልጆችን እንደ ወለደችልኝ እናንተ ታውቃላችሁ፤ 28አንዱም ከእኔ ወጣ፦ አውሬ በላው አላችሁኝ እስከ ዛሬም አላየሁትም፤ 29ይህንም ከእኔ ለይታችሁ ደግሞ ብትወስዱት ክፋም ቢያገኘው ሽበቴን በኅዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ። 30አሁንም እኔ ወደ አባቴ ወደ ባሪያህ ብሄድ ብላቴናውም ከእኛ ጋር ከሌለ ነፍሱ በብላቴናው ነፍስ ታስራለችና ብላቴናው ለእን ጋር እንደሌለ ባየ ጊዜ ይሞታል 31ባሪያዎህም የባሪያህን የአባታችንን ሽበት በኅዘን ወደ መቃብር ያወርዳሉ። 32እኔ ባሪያህ በአባቴ ዘንድ ስለ ብላቴናው እንዲህ ብዮ ተውሼአለሁና፦ እርሱንስ ወደ አንተ ባለመጣው በአባቴ ሀዘኔ በዘመናት ሁሉ ኃጢአተኛ እሆናለሁ። 33ስለዚህም እኔ ባሪያህ በጌታዬ ዘንድ ባሪያ ሆኜ በብላቴናው ፋንታ ልቀመጥ ብላቴናውም ከወንድሞቹ ጋር ይውጣ። 34አለዚያም ብላቴናው ከእኔ ጋር ከሌለ ወደ አባቴ እንዴት እወጣለሁ? አባቴን የሚያገኘውን መከራ እንዳላይ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ