ያዕቆብም ተነሥቶ ወደ ምሥራቅ ሰዎች አገር ሄደ። በሜዳውም እነሆ ጕድጓድም አየ በዚያም ሦስት የበጎች መንጎች በለዩ ተመስገው ነበር ከዚያ ጕድጓድ በጎቹን ያጠጡ ነበርና፤ በጕድጓዱም አፍ የነበረው ድንጋይ ትልቅ ነበረ። መንጎችም ሁሉ ከዚያ በተከማቹ ጊዜ ድንጋዩን ከጕድጓዱ አፍ ገለል አድርገው በጎቹን ያጠጡ ነበር ድንጋዩንም ወደ ስፍራው መልሰው በጕድጓዱ አፍ እንደ ገና ይገጥሙት ነበር። ያዕቆብም፦ ወንድሞቼ ሆይ እናንት የወዴት ናችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ እኛ የካራን ነን አሉት የናኮርን ልጅ ላባን ታውቁታላችሁን? አላቸው። እነርሱም፦ እናውቀዋለን አሉት። እርሱ፦ ደኅና ነው? አላቸው እነርሱም፦ አዎን ደኅና ነው፤ አሁንም ልጁ ራሔል ከበጎች ጋር መጣች አሉት። እርሱም፦ ቀኑ ገና ቀትር ነው ከብቶቹ የሚከማቹበት ሰዓቱም ገና አልደረሰም፤ አሁንም በጎቹን አጠጡና ሄዳችሁ አሰማሩምአቸው አላቸው። እነርሱም አሉ፦ መንጎች ሁሉ እስኪገለብጡት ድረስ አንችልም ከዚይም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን። እርሱም ገና ከእነርሱ ጋር ሲነጋገር እነሆ የላባ ልጅ ራሔል ከአባትዋ በጎች ጋር ደረስች እርስዋ የአባትዋን በጎች ትጠብቅ ነበርና። ያዕቆብም የእናቱን ወንድም የላባን ልጅ ራሔልንና የእጎቱን የላባን በጎች ባየ ጊዜ ቀረበ ከጕድጓድም አፍ ድንጋዩን ገለበጠ፥ የአጎቱን የላባን በጎችንም አጠጣ። ያዕቆብም ራሔልን ሳማት ቃሉንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ። ያዕቆብም የአባትዋ ዘመድና የርብቃ ልጅ መሆኑን ለራሔል አስታወቃት እርስዋም ሮጣ ሄዳ ለአባትዋ ይህን ነገር ነገርችው። ላባም የእኅቱን ልጅ የያዕቆብን ወሬ በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ሮጠ አቅፎም ሳመው ወደ ቤቱም አገባው። ነገሩንም ሁሉ ለላባ ነገረው። ላባም፦ በእውነት አንተ አጥንቴ ሥጋዬም ነህ አለው። አንድ ወር የሚያህልም ከእርሱ ጋር ተቀመጠ።
ኦሪት ዘፍጥረት 29 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 29:1-14
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች