የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 1:24-31

ኦሪት ዘፍጥረት 1:24-31 አማ54

እግዚአብሔርም አለ ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ ታዉጣ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ አደረገ እንስሳዉንም እንደ ወገኑ የመሬት ተንቀሳቃሾችም እንደ ወገኑ አደረገ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም አለ፤ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን እንስሳትንና ምድርን ሁ፤ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰዉን በመልኩ ፈጠረ በእግአብሔር መልክ ፈጠራቸዉ። እግዚአብሔርም ባረካቸዉ፤ እንዲህም አላቸው ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትም ሁሉ ግዙአቸዉ። እግዚአብሔርም አለ፤ እነሆ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ዘሩ በእርሱ ያለዉን ሐመለማል ሁሉ የዛፍን ፍሬ የሚያፈራዉንና ዘር ያለውንም ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ፤ ለምድርም አራዊት ሁሉ ለሰማይም ወፎች ሁሉ ሕያዉ ነፍስ ላላቸዉ ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ የሚበቅለው ሐመልማል ሁሉ መብል ይሁንላቸዉ እንዲሁም ሆነ። እግዚእብሔርም ያደረገዉን ሁሉ አየ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፤ ስድስተኚ ቀን።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}