መጽሐፈ መክብብ 4:7-12

መጽሐፈ መክብብ 4:7-12 አማ54

እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ከንቱ ነገር አየሁ። አንድ ሰው ብቻውን አለ፥ ሁለተኛም የለውም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፥ ለድካሙ ግን መጨረሻ የለውም፥ ዓይኖቹም ከባለጠግነት አይጠግቡም። ለማን እደክማለሁ፥ ሰውነቴንስ መልካሙን ነገር ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ክፉም ጥረት ነው። ድካማቸው መልካም ዋጋ አለውና አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል። ቢወድቁ አንዱ ሁለተኛውን ያነሣዋልና፥ አንዱ ብቻውን ሆኖ በወደቀ ጊዜ ግን የሚያነሣው ሁለተኛ የለውምና ወዮለት። ሁለቱም በአንድነት ቢተኙ ይሞቃቸዋል፥ አንድ ብቻውን ግን እንዴት ይሞቀዋል? አንዱም አንዱን ቢያሸንፍ ሁለቱ በፊቱ ይቆማሉ፥ በሦስትም የተገመደ ገመድ ፈጥኖ አይበጠስም።