በዚህ ዓለም ያለውን ሌላውንም ከንቱ ነገር ተመለከትኩ፤ እነሆ፥ ብቻውን የሚኖር አንድ ሰው አለ፤ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፤ ይሁን እንጂ ዘወትር በሥራ ከመድከም አይቦዝንም፤ ባገኘውም ሀብት በቃኝ ማለትን አላወቀም፤ “እርሱም የምደክመው ለማን ነው? ለራሴስ ደስታን የምነፍገው ለምንድን ነው?” ብሎ ራሱን ይጠይቃል፤ ይህ ሁሉ የባሰ ከንቱና የሥቃይ ሕይወት ነው። የሥራቸው ውጤት መልካም ሊሆን ስለሚችል አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል። ከሁለቱ አንዱ ቢወድቅ ሌላው ያነሣዋል፤ ብቻውን የሆነ ሰው ቢወድቅ እንኳ የሚያነሣው ረዳት ስለሌለው ወዮለት። ሁለቱ አብረው ቢተኙ ይሞቃቸዋል፤ ብቻውን የሚተኛ ሰው ግን እንዴት ሊሞቀው ይችላል? አንድ ሰው ብቻውን ሊመልሰው የማይችለውን አደጋ ሁለት ሰዎች ሊቋቋሙት ይችላሉ፤ በሦስት ተሸርቦ የተገመደ ፈትል እንኳ በቀላሉ አይበጠስም።
መጽሐፈ መክብብ 4 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መክብብ 4:7-12
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች