የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ጥበብ 18

18
ለእ​ስ​ራ​ኤል ብር​ሃን እንደ ወጣ​ላ​ቸው
1በጻ​ድ​ቃ​ንህ ዘንድ ግን ታላቅ ብር​ሃን ነበር፥ እነ​ዚያ ቃላ​ቸ​ውን ይሰሙ ነበ​ርና፥ መል​ካ​ቸ​ውን ግን አያ​ዩም ነበ​ርና።#ግሪኩ “ነገር ግን እነ​ርሱ የተ​ሠ​ቃ​ዩ​ትን ያህል ስላ​ል​ተ​ሠ​ቃዩ ደስ እንደ ተሰኙ ይቈ​ጥ​ሩ​አ​ቸው ነበር” የሚል ይጨ​ም​ራል። 2እነ​ዚያ የሚ​ወ​ዷ​ቸ​ውን ይደ​በ​ድ​ቧ​ቸው ነበ​ርና፤ የተ​በ​ደ​ሉ​ት​ንም መከራ ስለ አጸ​ኑ​ባ​ቸው እርስ በር​ሳ​ቸው ይመ​ሰ​ጋ​ገኑ ነበር።#ግሪኩ “ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው የበ​ደ​ሉ​አ​ቸ​ውን ሰዎች አመ​ሰ​ገ​ኑ​አ​ቸው፥ ምክ​ን​ያ​ቱም ስለ ፈጸ​ሙ​ባ​ቸው በደል አል​ተ​በ​ቀ​ሉ​አ​ቸ​ው​ምና፥ ሀገ​ራ​ቸ​ው​ንም ለቅ​ቀው እን​ዲ​ሄዱ ለመ​ኑ​አ​ቸው” ይላል። 3እነ​ዚህ ግን በተ​ላ​ከ​ላ​ቸው የማ​ዳን ስጦታ ደስ አላ​ቸው፥ የማ​ይ​ታ​ወቅ ጎዳ​ና​ንም ይመ​ራ​ቸው ዘንድ የእ​ሳት ዐም​ድን ሰጣ​ቸው፥ በሚ​ወ​ደ​ደ​ውም መን​ገድ የማ​ያ​ቃ​ጥል ፀሐ​ይን ሰጣ​ቸው። 4ብር​ሃ​ንን ያጡ ዘንድ፥ በጨ​ለ​ማም ይታ​ሰሩ ዘንድ ለእ​ነ​ዚያ ይገ​ባ​ቸ​ዋል፤ ለዓ​ለም ይሰጥ ዘንድ ያለው፥ የማ​ያ​ልፍ የሕ​ግህ ብር​ሃን ያላ​ቸው ልጆ​ች​ህን አስ​ረው አግ​ዘ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና።
የግ​ብ​ፃ​ው​ያን የበ​ኵር ልጆች ሞት
5የጻ​ድ​ቃን ልጆ​ችን ይገ​ድሉ ዘንድ ባሰ​ቡና በመ​ከሩ ጊዜ፥ ለዘ​ለፋ ሊሆ​ን​ባ​ቸው አንዱ ሕፃን ተጥሎ ዳነ። በእ​ር​ሱም ብዙ​ዎች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና ማኅ​በ​ራ​ቸ​ውን ሁሉ ያለ ርኅ​ራኄ በብዙ ውኃ አጠ​ፋህ። 6የተ​ማ​ማ​ሉ​ባ​ትን መሐላ ባወቁ ጊዜ፥ በፍ​ቅር ያስ​ቧት ዘንድ አባ​ቶ​ቻ​ችን ያቺን ሌሊት ዐወ​ቋት። 7ለጻ​ድ​ቃን ሕዝ​ብህ ደኅ​ን​ነ​ትን፥ ለተ​ቃ​ዋ​ሚ​ዎች ጠላ​ቶ​ችም ጥፋ​ትን ሰጠህ። 8የሚ​ቃ​ረ​ኑ​ትን እን​ዳ​ጠ​ፋ​ሃ​ቸው፥ እን​ዲሁ የጠ​ራ​ኸ​ንን እኛን አክ​ብ​ረ​ኸ​ና​ልና። 9አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጻድ​ቃን ያማረ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ይሠዉ ነበ​ረና፥ በመ​ስ​ማ​ማ​ትም የጌ​ት​ነ​ት​ህን ሕግ በል​ቡ​ና​ቸው አሳ​ድ​ረ​ዋ​ልና በዚህ አም​ሳል ቅዱ​ሳን መል​ካ​ሙን ነገር ተቀ​በሉ፥ መከ​ራ​ውም ለሚ​ገ​ባ​ቸው ነው። አባ​ቶ​ቻ​ችን ግን የም​ስ​ጋ​ና​ውን መዝ​ሙር በደ​ስታ ይዘ​ምሩ ነበር።
10ነገ​ራ​ቸው ሳይ​ተ​ባ​በር ከጠ​ላ​ቶች ልቅሶ ጩኸት ጋር ቃላ​ቸው ይገ​ናኝ ነበር። እና​ቶ​ችም ስለ ልጆ​ቻ​ቸው የል​ቅ​ሶ​ውን ድምፅ ያደ​ምጡ ነበር። 11የባ​ሪ​ያ​ውም ቅጣት ከጌ​ታው ጋር በመ​ቅ​ሠ​ፍት ተካ​ከለ። ጭፍ​ራ​ው​ንና ንጉ​ሡ​ንም ይህች መከራ እኩል አገ​ኘ​ቻ​ቸው። 12ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት በአ​ንድ አም​ሳል ሞቱ፤ ቍጥር የሌ​ላ​ቸው የሞቱ ሰዎች በድ​ኖ​ችም ነበሩ። በአ​ን​ዲት ሰዓት የከ​በ​ረች ፍጥ​ረ​ታ​ቸው ፈጽማ ስለ ጠፋች ሕያ​ዋን የሞ​ቱ​ትን ሰዎች ይቀ​ብ​ሯ​ቸው ዘንድ አል​ቻ​ሉ​ምና። 13ስለ ሟር​ታ​ቸ​ውም የመ​ጣ​ባ​ቸ​ውን መቅ​ሠ​ፍት ሁሉ አላ​ወ​ቁ​ምና በበ​ኸር ልጃ​ቸው መጥ​ፋት ሕዝቡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች እንደ ሆኑ ዐወቁ። 14ፍጹም ጸጥታ ፍጥ​ረ​ትን ሁሉ በሸ​ፈነ ጊዜ፥ ሌሊ​ቷም በፍ​ጥ​ነቷ መካ​ከል ሳለች፥ 15ሁሉን የሚ​ችል ቃልህ እንደ ድል አድ​ራ​ጊና ጦረኛ ሆኖ፥ ከሰ​ማ​ያት ከዙ​ፋ​ንህ ውስጥ ወደ ጥፋት ምድር መካ​ከል ወረደ። 16አድ​ልዎ የሌ​ለ​ባት ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንም እንደ ተሳለ ሰይፍ ታጥቆ፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ቆሞ አው​ራ​ጃ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ በሞት ሞላ፥ ሰማ​ይ​ንም ነካ፤ በም​ድ​ርም ቁሞ ነበር። 17ያን​ጊ​ዜም በአ​ስ​ፈ​ሪ​ዎች ሕል​ሞች ምት​ሀት አወ​ካ​ቸው፥ ያላ​ሳ​ቧት ድን​ጋ​ጤም በላ​ያ​ቸው ሠለ​ጠ​ነ​ች​ባ​ቸው። 18ከእ​ነ​ር​ሱም እኩ​ሌ​ታው የሞተ ሆኖ በሌላ ቦታ የሚ​ወ​ድቅ ነበረ፥ የሚ​ሞ​ቱ​ባ​ት​ንም ምክ​ን​ያት ገለ​ጠ​ላ​ቸው። 19ክፉ ነገር ስለ​ምን እን​ደ​ሚ​ያ​ገ​ኛ​ቸ​ውና እን​ደ​ሚ​ያ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም ባለ​ማ​ወቅ እን​ዳ​ይ​ሆኑ ያወ​ኳ​ቸው ሕል​ሞች አስ​ቀ​ድ​መው ይህን ነግ​ረ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና።
በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ስለ ታዘ​ዘው መቅ​ሠ​ፍት አሮን እንደ ጸለየ
20ከጻ​ድ​ቃ​ንም አስ​ቀ​ድሞ ለሞት የሚ​ያ​በቃ መከራ ያገ​ኛ​ቸው አሉ። በም​ድረ በዳም መቅ​ሠ​ፍት ሆነ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ብዙ​ዎ​ችን አጠፋ። ነገር ግን መቅ​ሠ​ፍቱ ብዙ ዘመን አል​ዘ​ገ​የም። 21ነውር የሌ​ለ​በት ሰው ጸሎት የሚ​ጸ​ል​ይ​በ​ትን፥ ዕጣ​ንም የሚ​ያ​ጥ​ን​በ​ትን የአ​ገ​ል​ግ​ሎት መሣ​ሪያ፥ ልብሰ መት​ከ​ፉን ይዞ ፈጥኖ ተዋ​ግ​ቶ​አ​ልና ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ለማ​ቃ​ለል ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን አገኘ፤ መዓ​ቱን ተቃ​ወመ፥ መቅ​ሠ​ፍ​ቱ​ንም ጸጥ አደ​ረገ። በዚ​ህም ያንተ መል​እ​ክ​ተኛ እንደ ሆነ ራሱን አስ​ታ​ወቀ። 22አጥ​ፊ​ዎ​ች​ንም አሸ​ነፈ፤ በሥ​ጋዊ ኀይል ወይም በጦር መሣ​ሪያ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን የአ​ባ​ቶ​ችን መሐ​ላና ቃል ኪዳ​ና​ቸ​ውን በማ​ሰብ ቀሣ​ፊ​ውን በቃ​ልህ አስ​ወ​ገደ። 23ብዛ​ታ​ቸው የማ​ይ​ቈ​ጠር የሞቱ ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው በወ​ደቁ ጊዜ በበ​ሽ​ተ​ኞ​ቹና በሕ​ያ​ዋ​ኖቹ መካ​ከል ቁሞ መቅ​ሠ​ፍ​ቱን ጸጥ አደ​ረገ። ለሕ​ያ​ዋ​ንም መን​ገ​ድን ለየ። 24የዓ​ለሙ ክህ​ነት ሁሉ በል​ብሱ ጫፍ ላይ ነበ​ርና፥ ባሕ​ርይ በሚ​ባሉ ዕን​ቍ​ዎች አራት ዙሪ​ያ​ዎች የተ​ቀ​ረ​ጸው የአ​በ​ውም ክብር በጫ​ን​ቃው ላይ ነበ​ርና፥ የአ​ን​ተም ልዕ​ልና በራሱ አክ​ሊል ላይ ነበ​ርና። 25በዚ​ህም የሚ​ያ​ጠፉ ቸነ​ፈ​ሮች ራቁ፥ እነ​ዚህ ሥራ​ዎ​ችም አስ​ፈ​ሯ​ቸው፥ ነገር ግን መቅ​ሠ​ፍቱ ብቻ በበቃ ነበር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ