መጽ​ሐፈ ጥበብ 14

14
የጣ​ዖት ከን​ቱ​ነት
1ዳግ​መ​ኛም ሰው በክፉ የባ​ሕር ማዕ​በል መካ​ከል ይሄድ ዘንድ ወድዶ በመ​ር​ከብ ላይ በወጣ ጊዜ ከም​ት​ሸ​ከ​መው ከመ​ር​ከ​ቢቱ፥ ከሚ​ዋ​ረ​ደ​ውና ከሚ​ደ​ክ​መው እን​ጨት ይለ​ም​ናል። 2ያን ጣዖት ትርፍ በመ​ው​ደድ ሠር​ቶ​ታ​ልና፥ ብል​ህም በብ​ል​ሀቱ ሠር​ቶ​ታ​ልና። 3አብ ሆይ፥ ያንተ አመ​ራር ግን ሁሉን ትሠ​ራ​ራ​ለች፤ በባ​ሕር ውስጥ መን​ገ​ድን፥ በሞ​ገ​ድም መካ​ከል ጽኑ መተ​ላ​ለ​ፊ​ያን ሰጥ​ተ​ሃ​ልና። 4ወደ መር​ከብ በማ​ው​ጣት፥ ዳግ​መ​ኛም ያለ ጥበብ ሰውን በባ​ሕር ላይ በማ​ሳ​ለፍ በእ​ው​ነት ሁሉን ማዳን እን​ደ​ሚ​ቻ​ልህ ታሳይ ዘንድ፥ 5የጥ​በ​ብህ ሥራው ስን​ፍና እን​ዳ​ይ​ሆን ትወ​ዳ​ለህ፥ ስለ​ዚህ ሰዎች ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን በተ​ና​ቀና በተ​ዋ​ረደ እን​ጨት ተማ​ም​ነው በታ​ላ​ቅና በታ​ናሽ መር​ከብ በሞ​ገዱ መካ​ከል ተሻ​ግ​ረው ይድ​ናሉ።
6ቀድ​ሞም ትዕ​ቢ​ተ​ኞች ረዓ​ይት#“ረዓ​ይት” ግዙ​ፋን ወፍ​ራ​ሞች ረዥ​ሞች ማለት ነው። በጠፉ ጊዜ የዓ​ለም ተስፋ በመ​ር​ከብ ተጭ​ኖና ተጠ​ግቶ ዳነ፥ በእ​ጅ​ህም ተመ​ርቶ የሰ​ውን ዘርዕ ለዓ​ለም አተ​ረፈ። 7ይህ መር​ከብ ጽድቅ ይሠ​ራ​በት ዘንድ ተባ​ር​ኳ​ልና። 8በእጅ የተ​ሠ​ራው ግን የሚ​ጠፋ ሲሆን አም​ላክ ስለ ተባለ የተ​ረ​ገመ ነው፤ የሠ​ራ​ውም ይህን በመ​ሥ​ራቱ ርጉም ነው። 9በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ክፉና ክፋቱ በት​ክ​ክል ተጠ​ል​ተ​ዋ​ልና፥ 10የተ​ሠ​ራው ሥራ ከሠ​ሪው ጋር ይፈ​ረ​ድ​በ​ታ​ልና። 11ስለ​ዚ​ህም በአ​ሕ​ዛብ ጣዖ​ታት ምር​መራ ይደ​ረ​ጋል። ፍጥ​ረ​ትን ለማ​ጥ​ፋት ለሰ​ዎ​ችም ነፍ​ሳት መሰ​ና​ክል፥ ለአ​ላ​ዋ​ቂ​ዎች ሰዎች እግ​ሮ​ችም ወጥ​መድ ሆኖ ተሠ​ር​ት​ዋ​ልና፥
ጣዖ​ትን ማም​ለክ የዝ​ሙት መጀ​መ​ሪያ ስለ መሆኑ
12የዝ​ሙት መጀ​መ​ሪ​ያዋ ጣዖ​ትን የመ​ሥ​ራት ዐሳብ ነውና፥ እር​ሱ​ንም ማግ​ኘት የሕ​ይ​ወት ጥፋት ነው። 13ከጥ​ንት ጀምሮ አል​ነ​በ​ረ​ምና ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም አይ​ኖ​ር​ምና። 14ተነ​ጥ​ቀው የመ​ሄ​ዳ​ቸ​ውን ፍጻሜ የሚ​ያ​ፋ​ጥን ስለ​ሆነ በከ​ንቱ ሰው ምክ​ን​ያት ጣዖት ወደ​ዚህ ዓለም ገባ። ከዚ​ህም በኋላ ጣዖት መሥ​ራ​ትን ዐሰቡ። 15ልጁ ሕፃን ሳለ ፈጥኖ በሞት ስለ ተነ​ጠቀ አባቱ ላንድ ልጁ ይጨ​ነ​ቅና ያለ​ቅስ ነበ​ርና፥ ቀድሞ ለሞ​ተው ልጁ ምስል ሠራ​ለት፥ ዛሬ ግን እንደ አም​ላክ አድ​ር​ገው አከ​በ​ሩት። ለኀ​ጢ​አት የተ​ገዙ ሰዎ​ችም በስ​ውር በዓል አደ​ረ​ጉ​ለት፥ የም​ሥ​ጢር መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም ሠዉ​ለት። 16ከዚህ በኋላ በዘ​መን መራቅ የበ​ደ​ልና የዝ​ን​ጋዔ ልማድ ሥር​ዐት ሆኖ ተያዘ፥ እንደ ሕግም አድ​ር​ገው ጠበ​ቁት፥ በክ​ፉ​ዎች መኳ​ን​ንት ትእ​ዛ​ዝም ጣዖ​ታ​ትን አመ​ለ​ኳ​ቸው። 17በሩቅ ስለ​ሚ​ኖሩ ፊት ለፊት ሊያ​ከ​ብ​ሯ​ቸው የማ​ይ​ቻ​ላ​ቸ​ውን ሰዎች ቅርፁ በሩቅ ያለ መል​ካ​ቸ​ውን ቀረፁ፥ በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ክቡር ለሚ​ሆን ለን​ጉ​ሡም ግልጥ የሆነ ምስል ሠሩ​ለት። የሌ​ለ​ው​ንም እን​ዳለ አድ​ር​ገው በት​ጋት ይለ​ም​ናሉ። 18ስሕ​ተ​ታ​ቸ​ው​ንም ያላ​ወቁ ሰዎች በአ​ም​ል​ኮ​ታ​ቸው ጸኑ። የጥ​በ​በ​ኛ​ው​ንም ክብር ወደ ጣዖት አም​ልኮ መለሱ። 19ዳግ​መኛ ገዥ​ውን ንጉሥ አድ​ልቶ ደስ ያሰ​ኘው ዘንድ የሚ​ወድ አለ። ባማ​ረና በተ​ሻለ ሁኔታ ምስ​ሉን ለመ​ሥ​ራት ተራ​ቅ​ቆ​አ​ልና። 20በሥ​ራ​ውም መልክ ማማር ደስ ስላ​ላ​ቸው ብዙ ሰዎች በዚህ ተሳቡ፥ ከጥ​ቂት ቀን አስ​ቀ​ድሞ በት​ንሽ ክብር የነ​በረ ሰው​ንም ዛሬ እንደ አም​ላክ አደ​ረ​ጉት። 21በች​ግር ወይም በግድ ሰው ሁሉ ተገ​ዝ​ት​ዋ​ልና ይህ ለሰው መሰ​ና​ክ​ልን ሆነ፤ ከእ​ነ​ርሱ ጋር አን​ድ​ነት የሌ​ለ​ውን የፈ​ጣ​ሪን ስም ለሚ​ጠ​ቀ​ሙ​ባ​ቸው ለድ​ን​ጋ​ይና እን​ጨት አድ​ር​ገ​ው​ታ​ልና።
የአ​ም​ልኮ ጣዖት ውጤት
22ዳግ​መ​ኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ካለ​ማ​ወ​ቃ​ቸው የተ​ነሣ ስሕ​ተ​ታ​ቸው አል​በ​ቃ​ቸ​ውም፥ ነገር ግን በታ​ላቅ ሰልፍ ሳሉ በስ​ን​ፍ​ና​ቸው ይኖ​ራሉ። ይህን ያህል ክፉ የሆ​ነ​ው​ንም ታላቅ አደ​ረጉ፥ ሰላም ብለ​ውም ጠሩት። 23ልጆ​ቻ​ቸ​ውን የሚ​ሠዉ አሉና፤ የተ​ሰ​ወረ ምሥ​ጢ​ር​ንም ያደ​ር​ጋሉ፥ በልዩ ሥር​ዐ​ትም እየ​ተ​ቅ​በ​ዘ​በዙ ያስ​ባሉ። 24ሕጋ​ቸ​ው​ንና ጋብ​ቻ​ቸ​ውን አል​ጠ​በ​ቁም፤ ነገር ግን ባል​ን​ጀራ ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ይገ​ድ​ለ​ዋል፤ ያም ባይ​ሆን ያባ​ብ​ለ​ዋል፥ በሽ​ተ​ኛም ያደ​ር​ገው ዘንድ ተስፋ ይሰ​ጠ​ዋል። 25ሥራ​ዎ​ቻ​ቸው ሁሉ ደም ከማ​ፍ​ሰ​ስና ነፍስ ከመ​ግ​ደል ጋር፥ ከመ​ስ​ረ​ቅም ጋር፥ ከሐ​ሰ​ትና ከጥ​ፋት፥ ምስ​ጋ​ና​ንም ከማ​ጕ​ደል ጋር፥ ካለ​ማ​መ​ንም ጋር፥ ከመ​ሐ​ላና በጎ​ውን ሰው ከማ​ወክ ጋር፥ 26ዋጋን ካለ​ማ​ሰብ ጋር፥ ሰው​ነ​ትን ከማ​ስ​ተ​ዳ​ደፍ ጋር፥ ፍጥ​ረ​ት​ንም ከመ​ለ​ወጥ ጋር፥ የጋ​ብ​ቻን ሥር​ዐት ከማ​ፍ​ረስ ጋር፥ ከም​ን​ዝ​ርና ከር​ኵ​ሰት ጋር፥ የተ​ቀ​ላ​ቀለ ነው። 27ስም የሌ​ላ​ቸው ጣዖ​ቶ​ችን ማም​ለክ የክ​ፋት ሁሉ መጀ​መ​ሪያ ነውና፥ የፍ​ጻ​ሜ​ውም ምክ​ን​ያት ነውና። 28የሚ​ያ​መ​ል​ኳ​ቸው ሰዎች እንደ እነ​ዚህ ደስ ቢላ​ቸው አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን ያጣ​ሉና። ያም ባይ​ሆን በሐ​ሰት ትን​ቢት ይና​ገ​ራሉ፥ ያም ባይ​ሆን ይሙት በቃ​ውን ያድ​ናሉ፥ ያም ባይ​ሆን ፈጥ​ነው ይም​ላሉ። 29ቃልና ዕው​ቀት ያላ​ቸው እነ​ዚህ ሁሉን እን​ደ​ሚ​ያ​ውቅ እንደ ፈጣሪ አድ​ር​ገው ነፍስ የሌ​ለው ሐሰ​ተ​ኛና ድዳ ጣዖ​ትን ይታ​መ​ናሉ፥ ቢም​ሉም እን​ደ​ሚ​ፈ​ረ​ድ​ባ​ቸው አያ​ስ​ቡም። 30እው​ነ​ተኛ ፍርድ በአ​ን​ድ​ነት ያገ​ኛ​ቸ​ዋል፥ ጣዖ​ቱን በተ​መ​ለ​ከቱ ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክፉ ነገ​ርን ዐስ​በ​ዋ​ልና፥ የፈ​ጣ​ሪን እው​ነት አቃ​ል​ለው በግ​ፍና በሐ​ሰት ምለ​ው​በ​ታ​ልና። 31በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው የተ​ፈ​ረ​ደ​ባ​ቸ​ውን ፍርድ ለማ​ስ​ተ​ላ​ለፍ ነው እንጂ ኀይ​ሉን ይገ​ል​ጥ​ብ​ናል ሲሉ የማሉ አይ​ደ​ለ​ምና፤ እን​ግ​ዲህ ሁል​ጊዜ ሰውን በሚ​በ​ድሉ ሰዎች ወን​ጀል ላይ ፍርድ ትም​ጣ​ባ​ቸው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

YouVersion የእርስዎን ተሞክሮ ግላዊ ለማድረግ ኩኪዎችን ይጠቀማል። የእኛን ድረ ገጽ በመጠቀም፣ በግለሰብነት መመሪያችን ላይ እንደተገለጸው የእኛን የኩኪዎች አጠቃቀም ተቀብለዋል