የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 96

96
ምድሩ በተ​መ​ለ​ሰች ጊዜ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገሠ፥ ምድር ሐሤ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለች፥
ብዙ ደሴ​ቶ​ችም ደስ ይላ​ቸ​ዋል።
2ደመ​ናና ጭጋ​ግም በዙ​ሪ​ያው ናቸው፤
ፍት​ሕና ርትዕ የዙ​ፋኑ መሠ​ረት ናቸው፤
3እሳት በፊቱ ይሄ​ዳል፥
ነበ​ል​ባ​ሉም ጠላ​ቶ​ቹን ይከ​ብ​ባ​ቸ​ዋል።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ጠላ​ቶ​ቹን በዙ​ሪ​ያው ያቃ​ጥ​ላል” ይላል።
4መብ​ረ​ቆቹ ለዓ​ለም አበሩ፤
ምድር ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች#ዕብ. “አየች” ይላል። ተና​ወ​ጠ​ችም።
5ተራ​ሮ​ችም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ እንደ ሰም ቀለጡ፥
ምድር ሁሉ ከአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ ቀለ​ጠች።
6ሰማ​ያት የእ​ር​ሱን ጽድቅ አወሩ፥
አሕ​ዛ​ብም ሁሉ ክብ​ሩን አዩ።
7ለተ​ቀ​ረጸ ምስል የሚ​ሰ​ግዱ ሁሉ፥
በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የሚ​መኩ ይፈሩ፤
መላ​እ​ክ​ቱም ሁሉ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል።
8አቤቱ፥ ስለ ፍር​ድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥
የይ​ሁ​ዳም ሴቶች ልጆች ሐሤት አደ​ረጉ፤
9አንተ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ በም​ድር ላይ ሁሉ ብቻ​ህን ልዑል ነህና፥
በአ​ማ​ል​ክ​ትም ሁሉ ላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለ​ሃ​ልና።
10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ወ​ድዱ፥ ክፋ​ትን ጥሉ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጻ​ድ​ቃ​ኑን ነፍ​ሶች ይጠ​ብ​ቃል፥
ከኃ​ጥ​ኣ​ንም እጅ ያድ​ና​ቸ​ዋል።
11ብር​ሃን ለጻ​ድ​ቃን፥
ደስ​ታም ለልበ ቅኖች ወጣ።
12ጻድ​ቃን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይላ​ቸ​ዋል።
ለቅ​ድ​ስ​ና​ውም መታ​ሰ​ቢያ ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ