መዝሙረ ዳዊት 96
96
ምድሩ በተመለሰች ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔር ነገሠ፥ ምድር ሐሤትን ታደርጋለች፥
ብዙ ደሴቶችም ደስ ይላቸዋል።
2ደመናና ጭጋግም በዙሪያው ናቸው፤
ፍትሕና ርትዕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው፤
3እሳት በፊቱ ይሄዳል፥
ነበልባሉም ጠላቶቹን ይከብባቸዋል።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ጠላቶቹን በዙሪያው ያቃጥላል” ይላል።
4መብረቆቹ ለዓለም አበሩ፤
ምድር ተንቀጠቀጠች#ዕብ. “አየች” ይላል። ተናወጠችም።
5ተራሮችም ከእግዚአብሔር ፊት የተነሣ እንደ ሰም ቀለጡ፥
ምድር ሁሉ ከአግዚአብሔር ፊት የተነሣ ቀለጠች።
6ሰማያት የእርሱን ጽድቅ አወሩ፥
አሕዛብም ሁሉ ክብሩን አዩ።
7ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥
በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ፤
መላእክቱም ሁሉ ይሰግዱለታል።
8አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥
የይሁዳም ሴቶች ልጆች ሐሤት አደረጉ፤
9አንተ፥ እግዚአብሔር፥ በምድር ላይ ሁሉ ብቻህን ልዑል ነህና፥
በአማልክትም ሁሉ ላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለሃልና።
10እግዚአብሔርን የምትወድዱ፥ ክፋትን ጥሉ፤
እግዚአብሔር የጻድቃኑን ነፍሶች ይጠብቃል፥
ከኃጥኣንም እጅ ያድናቸዋል።
11ብርሃን ለጻድቃን፥
ደስታም ለልበ ቅኖች ወጣ።
12ጻድቃን በእግዚአብሔር ደስ ይላቸዋል።
ለቅድስናውም መታሰቢያ ያመሰግናሉ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 96: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ