መዝሙረ ዳዊት 87
87
የቆሬ ልጆች የምስጋና መዝሙር። ለመዘምራን አለቃ በማኸላት ለመዘመር የይዝራኤላዊው የኤማን ትምህርት።
1የድኅነቴ አምላክ እግዚአብሔር፥
በቀንና በሌሊት በፊትህ ጮኽሁ፤
2ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትግባ፥
ጆሮህንም ወደ ልመናዬ አዘንብል፤
3ነፍሴ መከራን ጠግባለችና፥
ሕይወቴም ለሞት ቀርባለችና።
4ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተቈጠርሁ፥
ረዳትም እንደሌለው ሰው ሆንሁ።
5እንደ ተገደሉና በመቃብር ውስጥ እንደ ተጣሉ፥
ለዘለዓለም እንደማታስባቸው
በሙታን መካከል የተጣልሁ ሆንሁ፤
እነርሱ ከእጅህ ርቀዋልና።
6በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ፥
በታችኛው ጕድጓድ አስቀመጡኝ።#ዕብ. “አስቀመጥኸኝ” ይላል።
7በእኔ ላይ ቍጣህ ጸና፥
መቅሠፍትህን ሁሉ በእኔ ላይ አመጣህ።
8የሚያውቁኝን ከእኔ አራቅህ፤
በእነርሱ ዘንድ ርኩስ አደረግኸኝ፤
ያዙኝ፥ መውጫም የለኝም።
9ዐይኖቼም በችግር ፈዘዙ፤
አቤቱ፥ ሁልጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥
እጆቼንም ወደ አንተ ዘረጋሁ።
10በውኑ ለሙታን ድንቅን ታደርጋለህን?
ወይስ ያመሰግኑህ ዘንድ ባለ መድኀኒቶች ያነሡአቸዋልን?
11በመቃብርስ ውስጥ ያሉት ቸርነትህን፥
እውነትህንስ በሞት ስፍራ ይናገራሉን?
12ተአምራትህ በጨለማ ይታወቃልን?
ቅንነትህስ በምድር ተረሳን?#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በመርሳት ምድር” ይላል።
13አቤቱ፥ እኔ ግን ወደ አንተ ጮኽሁ፤
በጥዋት ጸሎቴ ወደ አንተ ትድረስ።
14አቤቱ፥ ጸሎቴን#ዕብ. “ነፍሴን” ይላል። ለምን ትጥላለህ?
ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትመልሳለህ።#ዕብ. “ትሰውራለህን?” ይላል።
15እኔ ድሃ ነኝ፥ ከሕፃንነቴ ጀምሮ ደከምሁ።
ከፍ ከፍ ካልሁ በኋላ ተዋረድሁ፥ ተናቅሁም።
16መቅሠፍት በላዬ አለፈ፥
ግርማህም አስደነገጠኝ።
17ሁልጊዜ እንደ ውኃ ከበቡኝ፥
በአንድነትም ያዙኝ።
18ወዳጆቼንና ባልንጀሮቼን
ዘመዶቼንም ከችግሬ የተነሣ ከእኔ አራቅህ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 87: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ