የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 87

87
የቆሬ ልጆች የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር። ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ በማ​ኸ​ላት ለመ​ዘ​መር የይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው የኤ​ማን ትም​ህ​ርት።
1የድ​ኅ​ነቴ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥
በቀ​ንና በሌ​ሊት በፊ​ትህ ጮኽሁ፤
2ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትግባ፥
ጆሮ​ህ​ንም ወደ ልመ​ናዬ አዘ​ን​ብል፤
3ነፍሴ መከ​ራን ጠግ​ባ​ለ​ችና፥
ሕይ​ወ​ቴም ለሞት ቀር​ባ​ለ​ችና።
4ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ተቈ​ጠ​ርሁ፥
ረዳ​ትም እን​ደ​ሌ​ለው ሰው ሆንሁ።
5እንደ ተገ​ደ​ሉና በመ​ቃ​ብር ውስጥ እንደ ተጣሉ፥
ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ደ​ማ​ታ​ስ​ባ​ቸው
በሙ​ታን መካ​ከል የተ​ጣ​ልሁ ሆንሁ፤
እነ​ርሱ ከእ​ጅህ ርቀ​ዋ​ልና።
6በጨ​ለ​ማና በሞት ጥላ ውስጥ፥
በታ​ች​ኛው ጕድ​ጓድ አስ​ቀ​መ​ጡኝ።#ዕብ. “አስ​ቀ​መ​ጥ​ኸኝ” ይላል።
7በእኔ ላይ ቍጣህ ጸና፥
መቅ​ሠ​ፍ​ት​ህን ሁሉ በእኔ ላይ አመ​ጣህ።
8የሚ​ያ​ው​ቁ​ኝን ከእኔ አራ​ቅህ፤
በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ርኩስ አደ​ረ​ግ​ኸኝ፤
ያዙኝ፥ መው​ጫም የለ​ኝም።
9ዐይ​ኖቼም በች​ግር ፈዘዙ፤
አቤቱ፥ ሁል​ጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥
እጆ​ቼንም ወደ አንተ ዘረ​ጋሁ።
10በውኑ ለሙ​ታን ድን​ቅን ታደ​ር​ጋ​ለ​ህን?
ወይስ ያመ​ሰ​ግ​ኑህ ዘንድ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶች ያነ​ሡ​አ​ቸ​ዋ​ልን?
11በመ​ቃ​ብ​ርስ ውስጥ ያሉት ቸር​ነ​ት​ህን፥
እው​ነ​ት​ህ​ንስ በሞት ስፍራ ይና​ገ​ራ​ሉን?
12ተአ​ም​ራ​ትህ በጨ​ለማ ይታ​ወ​ቃ​ልን?
ቅን​ነ​ት​ህስ በም​ድር ተረ​ሳን?#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በመ​ር​ሳት ምድር” ይላል።
13አቤቱ፥ እኔ ግን ወደ አንተ ጮኽሁ፤
በጥ​ዋት ጸሎቴ ወደ አንተ ትድ​ረስ።
14አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን#ዕብ. “ነፍ​ሴን” ይላል። ለምን ትጥ​ላ​ለህ?
ፊት​ህ​ንስ ከእኔ ለምን ትመ​ል​ሳ​ለህ።#ዕብ. “ትሰ​ው​ራ​ለ​ህን?” ይላል።
15እኔ ድሃ ነኝ፥ ከሕ​ፃ​ን​ነቴ ጀምሮ ደከ​ምሁ።
ከፍ ከፍ ካልሁ በኋላ ተዋ​ረ​ድሁ፥ ተና​ቅ​ሁም።
16መቅ​ሠ​ፍት በላዬ አለፈ፥
ግር​ማ​ህም አስ​ደ​ነ​ገ​ጠኝ።
17ሁል​ጊዜ እንደ ውኃ ከበ​ቡኝ፥
በአ​ን​ድ​ነ​ትም ያዙኝ።
18ወዳ​ጆ​ቼ​ንና ባል​ን​ጀ​ሮ​ቼን
ዘመ​ዶ​ቼ​ንም ከች​ግሬ የተ​ነሣ ከእኔ አራ​ቅህ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ