የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 86

86
የቆሬ ልጆች የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር።
1መሠ​ረ​ቶ​ችዋ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “መሰ​ረ​ቶቹ” ይላል። በተ​ቀ​ደሱ ተራ​ሮች ናቸው፤
2ከያ​ዕ​ቆብ ድን​ኳ​ኖች ይልቅ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ዮ​ንን ደጆች ይወ​ድ​ዳ​ቸ​ዋል።
3የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተማ ሆይ፥ ስለ አንቺ
የተ​ነ​ገ​ረው ነገር ድንቅ ነው።
4የሚ​ያ​ው​ቁ​ኝን ረዓ​ብ​ንና ባቢ​ሎ​ንን አስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤
እነሆ፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን፥ ጢሮ​ስም የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያም ሕዝብ፥
እነ​ዚህ በዚያ ተወ​ለዱ።
5ሰው እና​ታ​ችን ጽዮን ይላል፥
በው​ስ​ጥ​ዋም ሰው ተወ​ለደ፤
እርሱ ራሱም ልዑል መሠ​ረ​ታት።
6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ፥
በው​ስ​ጥ​ዋም ለተ​ወ​ለ​ዱት አለ​ቆ​ችዋ በመ​ጽ​ሐፍ ይነ​ግ​ራ​ቸ​ዋል።
7በአ​ንቺ የሚ​ኖሩ ሁሉ ደስ እን​ደ​ሚ​ላ​ቸው ይነ​ግ​ራ​ቸ​ዋል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ