መዝሙረ ዳዊት 86
86
የቆሬ ልጆች የምስጋና መዝሙር።
1መሠረቶችዋ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “መሰረቶቹ” ይላል። በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፤
2ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ፥
እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል።
3የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፥ ስለ አንቺ
የተነገረው ነገር ድንቅ ነው።
4የሚያውቁኝን ረዓብንና ባቢሎንን አስባቸዋለሁ፤
እነሆ፥ ፍልስጥኤማውያን፥ ጢሮስም የኢትዮጵያም ሕዝብ፥
እነዚህ በዚያ ተወለዱ።
5ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥
በውስጥዋም ሰው ተወለደ፤
እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።
6እግዚአብሔር ለሕዝቡ፥
በውስጥዋም ለተወለዱት አለቆችዋ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል።
7በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 86: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ