መዝሙረ ዳዊት 26
26
ሳይቀባ፥ የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔር ያበራልኛል፥ ያድነኛልም፤
ምን ያስፈራኛል? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤
ምን ያስደነግጠኛል?
2ክፉዎች ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ በቀረቡ ጊዜ፥
የሚያሠቃዩኝ እነዚያ ጠላቶቼ ደከሙ፥ ወደቁም።
3ሠራዊትም ቢጠላኝ ልቤ አይፈራብኝም፤
ሠራዊትም#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰልፍ ቢነሣብኝ” ይላሉ። ቢከቡኝ በእርሱ እተማመናለሁ።
4እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት፥ እርስዋንም እሻለሁ፤
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥
እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥
በቤተ መቅደሱም አገለግል ዘንድ።
5በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ሸሽጎኛልና፥
በድንኳኑም መሸሸጊያ ሰውሮኛልና፥
በዓለትም ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና።
6እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፤
ዞርሁ በድንኳኑም መሥዋዕትን ሠዋሁ፥ እልልም አልሁለት
እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፥ እዘምርለትማለሁ።
7አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን ቃሌን ስማኝ፤
ማረኝ፥ አድምጠኝም።
8ልቤ አንተን አለ፦
ፊትህን ፈለግሁ፥
አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ።
9ፊትህን ከእኔ አትመልስ፥
ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤
ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥
አምላኪዬና መድኀኒቴ ሆይ፥ ቸል አትበለኝ።
10አባቴና እናቴ ጥለውኛልና፥
እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ።
11አቤቱ መንገድህን አስተምረኝ፥
ስለ ጠላቶቼም በቀና መንገድ ምራኝ።
12ለሚያስጨንቁኝ ፈቃድ አትስጠኝ፥
የዐመፅ ምስክሮች ተነሥተውብኛልና፥
ሐሰትም የዐመፅ ራስ ነው።
13የእግዚአብሔርን ቸርነት በሕያዋን ምድር
አይ ዘንድ አምናለሁ።
14እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤
በርታ፥ ልብህንም አጽና፤
እግዚአብሔርንም ተስፋ አድርግ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 26: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ