የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 26

26
ሳይ​ቀባ፥ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያበ​ራ​ል​ኛል፥ ያድ​ነ​ኛ​ልም፤
ምን ያስ​ፈ​ራ​ኛል? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሕ​ይ​ወቴ መታ​መ​ኛዋ ነው፤
ምን ያስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ኛል?
2ክፉ​ዎች ሥጋ​ዬን ይበሉ ዘንድ በቀ​ረቡ ጊዜ፥
የሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩኝ እነ​ዚያ ጠላ​ቶቼ ደከሙ፥ ወደ​ቁም።
3ሠራ​ዊ​ትም ቢጠ​ላኝ ልቤ አይ​ፈ​ራ​ብ​ኝም፤
ሠራ​ዊ​ትም#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰልፍ ቢነ​ሣ​ብኝ” ይላሉ። ቢከ​ቡኝ በእ​ርሱ እተ​ማ​መ​ና​ለሁ።
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አን​ዲት ነገር ለመ​ን​ሁት፥ እር​ስ​ዋ​ንም እሻ​ለሁ፤
በሕ​ይ​ወቴ ዘመን ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እኖር ዘንድ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ው​ንም አይ ዘንድ፥
በቤተ መቅ​ደ​ሱም አገ​ለ​ግል ዘንድ።
5በመ​ከ​ራዬ ቀን በድ​ን​ኳኑ ሸሽ​ጎ​ኛ​ልና፥
በድ​ን​ኳ​ኑም መሸ​ሸ​ጊያ ሰው​ሮ​ኛ​ልና፥
በዓ​ለ​ትም ላይ ከፍ ከፍ አድ​ር​ጎ​ኛ​ልና።
6እነሆ፥ አሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጠ​ላ​ቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደ​ረገ፤
ዞርሁ በድ​ን​ኳ​ኑም መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋሁ፥ እል​ልም አል​ሁ​ለት
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ እዘ​ም​ር​ለ​ት​ማ​ለሁ።
7አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮ​ኽ​ሁ​ትን ቃሌን ስማኝ፤
ማረኝ፥ አድ​ም​ጠ​ኝም።
8ልቤ አን​ተን አለ፦
ፊት​ህን ፈለ​ግሁ፥
አቤቱ፥ ፊት​ህን እሻ​ለሁ።
9ፊት​ህን ከእኔ አት​መ​ልስ፥
ተቈ​ጥ​ተህ ከባ​ሪ​ያህ ፈቀቅ አት​በል፤
ረዳት ሁነኝ፥ አት​ጣ​ለ​ኝም፥
አም​ላ​ኪ​ዬና መድ​ኀ​ኒቴ ሆይ፥ ቸል አት​በ​ለኝ።
10አባ​ቴና እናቴ ጥለ​ው​ኛ​ልና፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ተቀ​በ​ለኝ።
11አቤቱ መን​ገ​ድ​ህን አስ​ተ​ም​ረኝ፥
ስለ ጠላ​ቶ​ቼም በቀና መን​ገድ ምራኝ።
12ለሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ፈቃድ አት​ስ​ጠኝ፥
የዐ​መፅ ምስ​ክ​ሮች ተነ​ሥ​ተ​ው​ብ​ኛ​ልና፥
ሐሰ​ትም የዐ​መፅ ራስ ነው።
13የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቸር​ነት በሕ​ያ​ዋን ምድር
አይ ዘንድ አም​ና​ለሁ።
14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ አድ​ርግ፤
በርታ፥ ልብ​ህ​ንም አጽና፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ተስፋ አድ​ርግ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ