መዝሙረ ዳዊት 146
146
የሐጌና የዘካርያስ መዝሙር።
ሃሌ ሉያ።
1እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ መዝሙር መልካም ነውና።
ለአምላካችንም ምስጋና ማቅረብ ያማረ ነው።
2እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ይሠራታል፥
ከእስራኤልም የተበተኑትን ይሰበስባል።
3ልባቸው የቈሰለውን ይፈውሳል፥
ቍስላቸውንም ያደርቅላቸዋል።
4ከዋክብትንም በሙሉ ይቈጥራቸዋል፥
ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል።
5እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥
ኀይሉም ታላቅ ነው፥ ለጥበቡም ቍጥር የለውም።
6እግዚአብሔር የዋሃንን ያነሣቸዋል፥
ኃጥአንን ግን እስከ ምድር ድረስ ያዋርዳቸዋል።
7ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፥#ግእዝ “ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር በአሚን” ይላል።
ለአምላካችንም በመሰንቆ ዘምሩ፤
8ሰማዩን በደመናት የሚሸፍን፥
ለምድርም ዝናምን የሚያዘጋጅ፥
ሣርን በተራሮች ላይ፥
ልምላሜውንም ለሰው ልጆች አገልግሎት የሚያበቅል፥
9ለእንስሶችና ለሚጠሩት ለቍራዎች ጫጩቶች፥
ምግባቸውን የሚሰጣቸው እርሱ ነው።
10የፈረስን ኀይል አይወድድም፥
በሰውም ጕልበት ደስ አይለውም።
11እግዚአብሔር በሚፈሩት፥
በምሕረቱም በሚታመኑ ደስ ይለዋል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 146: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ