የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 145

145
የሐ​ጌና የዘ​ካ​ር​ያስ መዝ​ሙር።
ሃሌ ሉያ።
1ነፍሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች።
2በሕ​ይ​ወቴ ሳለሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ፤
በም​ኖ​ር​በት ዘመን መጠን ለአ​ም​ላኬ እዘ​ም​ራ​ለሁ።
3ማዳን በማ​ይ​ችሉ በአ​ለ​ቆ​ችና በሰው ልጆች አት​ታ​መኑ።
4ነፍ​ሳ​ቸው ትወ​ጣ​ለች፥ ወደ መሬ​ትም ይመ​ለ​ሳሉ፤
ያን​ጊዜ ምክ​ራ​ቸው#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዐሳ​ባ​ቸው” ይላል። ሁሉ ይጠ​ፋል።
5የያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ ረዳቱ የሆነ፥
መታ​መ​ኛ​ውም በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆነ ሰው ብፁዕ ነው።
6እር​ሱም ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ባሕ​ር​ንም፥ በእ​ነ​ርሱ ውስጥ ያለ​ው​ንም ሁሉ የፈ​ጠረ፤
እው​ነ​ትን ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ጠ​ብቅ፤
7ለተ​በ​ደ​ሉ​ትም የሚ​ፈ​ር​ድ​ላ​ቸው፥
ለተ​ራቡ ምግ​ብን የሚ​ሰጥ ነው።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​ሰ​ሩ​ትን ይፈ​ታ​ቸ​ዋል፤
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የወ​ደ​ቁ​ትን ያነ​ሣ​ቸ​ዋል፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዕው​ሮ​ችን ጥበ​በ​ኞች ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድ​ቃ​ንን ይወ​ድ​ዳ​ቸ​ዋል፤
9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስደ​ተ​ኞ​ችን ይጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋል፤
ድሃ አደ​ጎ​ች​ንና ባል​ቴ​ቶ​ችን ይቀ​በ​ላ​ቸ​ዋል፤
የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም መን​ገድ ያጠ​ፋል።
10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይነ​ግ​ሣል፤
ጽዮን ሆይ፥ አም​ላ​ክሽ ለልጅ ልጅ ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ