መዝሙረ ዳዊት 147
147
የሐጌና የዘካርያስ መዝሙር።
ሃሌ ሉያ።
1ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግዚአብሔርን አመስግኚ፥
2ጽዮንም ሆይ፥ አምላክሽን አመስግኚ፤
የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፥
ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኮአልና።
3ለወሰኖችሽም ሰላምን አደረገ፥
የስንዴንም ስብ አጠገበሽ።
4ቃሉን ወደ ምድር ይልካል፥
ነገሩም እጅግ ፈጥኖ ይሮጣል።
5በረዶውን እንደ ባዘቶ ይሰጣል፤
ጉሙን እንደ አመድ ይበትነዋል፤
6በረዶውን እንደ ፍርፋሪ ያወርዳል፤
ቅዝቃዜውንስ ማን ይቋቋማል?
7ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል፤
ነፋሱን ያነፍሳል፥ ውኆችንም ያፈስሳል።
8ቃሉን ለያዕቆብ፥
ሥርዐቱንና ፍርዱንም ለእስራኤል ይናገራል።
9ለሌሎች አሕዛብ ሁሉ እንዲህ አላደረገም፥
ፍርዱንም አልገለጠላቸውም።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 147: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ