መዝ​ሙረ ዳዊት 135

135
ሃሌ ሉያ።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፥ ቸር ነውና፥
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።
2የአ​ማ​ል​ክ​ትን አም​ላክ አመ​ስ​ግኑ፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።
3የጌ​ቶ​ችን ጌታ አመ​ስ​ግኑ፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
4እርሱ ብቻ​ውን ታላቅ ተአ​ም​ራ​ትን ያደ​ረገ፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
5ሰማ​ያ​ትን በጥ​በቡ የሠራ፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
6ምድ​ርን በውኃ ላይ ያጸና፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
7ብቻ​ውን ታላ​ላቅ ብር​ሃ​ና​ትን የሠራ፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
8ለፀ​ሐይ ቀንን ያስ​ገ​ዛው፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
9ለጨ​ረ​ቃና ለከ​ዋ​ክ​ብት ሌሊ​ትን ያስ​ገ​ዛ​ቸው፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
10ከበ​ኵ​ራ​ቸው ጋር ግብ​ፅን የገ​ደለ፥
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
11እስ​ራ​ኤ​ልን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ያወጣ፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
12በጸ​ናች እጅ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
13የኤ​ር​ት​ራን ባሕር ፈጽሞ የከ​ፈለ፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
14እስ​ራ​ኤ​ልን በመ​ካ​ከሉ ያሳ​ለፈ፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
15ፈር​ዖ​ን​ንና ሠራ​ዊ​ቱን በኤ​ር​ትራ ባሕር ውስጥ የጣለ፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
16ሕዝ​ቡን በም​ድረ በዳ የመራ፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
ከዓ​ለት ውኃን ያፈ​ለቀ፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤#“ከዓ​ለት ውኃን ያፈ​ለቀ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና” የሚ​ለው በዕብ. የለም።
17ታላ​ላቅ ነገ​ሥ​ታ​ትን የገ​ደለ፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
18ጽኑ​ዓን ነገ​ሥ​ታ​ትን የገ​ደለ፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
19የአ​ሞ​ራ​ው​ያ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፥
20የባ​ሳ​ንን ንጉሥ ዐግን፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
21ርስት ምድ​ራ​ቸ​ውን
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፥
ለባ​ሪ​ያው ለእ​ስ​ራ​ኤል ርስት አድ​ርጎ የሰጠ፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኛን በመ​ዋ​ረ​ዳ​ችን ዐስ​ቦ​ና​ልና፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
23ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ንም እጅ አድ​ኖ​ና​ልና፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤
24ለሥጋ ሁሉ ምግ​ብን የሚ​ሰጥ፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።
25የሰ​ማ​ይን አም​ላክ አመ​ስ​ግኑ፤
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ