የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 134

134
ሃሌ ሉያ።
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም አመ​ስ​ግኑ፤
እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪ​ያ​ዎች ሆይ፥ አመ​ስ​ግ​ኑት።
2በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ፥
በአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት አደ​ባ​ባይ የም​ት​ቆሙ።
3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤
ለስሙ ዘምሩ፥ መል​ካም ነውና፤
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዕ​ቆ​ብን ለራሱ፥
እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ርስቱ እን​ዲ​ሆን መር​ጦ​ታ​ልና፤
5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ እንደ ሆነ፥
አም​ላ​ካ​ች​ንም ከአ​ማ​ል​ክት ሁሉ እን​ዲ​በ​ልጥ አው​ቃ​ለ​ሁና።
6በሰ​ማ​ይና በም​ድር፥ በባ​ሕ​ርና በጥ​ል​ቆ​ችም ሁሉ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የወ​ደ​ደ​ውን ሁሉ አደ​ረገ።
7ከም​ድር ዳር ደመ​ና​ትን ያወ​ጣል፤
ለዝ​ናም ጊዜም መብ​ረ​ቅን አደ​ረገ፤
ነፋ​ሳ​ት​ንም ከመ​ዛ​ግ​ብቱ#ግእዝ “እመ​ዛ​ግ​ብ​ቲ​ሆሙ” ይላል። ያወ​ጣል።
8የግ​ብ​ፅን በኵር ልጆች ሁሉ
ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ ድረስ ገደለ።
9ግብፅ ሆይ፥ በመ​ካ​ከ​ልሽ በፈ​ር​ዖ​ንና በባ​ሪ​ያ​ዎቹ ሁሉ ላይ
ተአ​ም​ራ​ት​ንና ድን​ቅን ሰደደ።
10ብዙ አሕ​ዛ​ብን መታ፥
ብር​ቱ​ዎ​ች​ንም ነገ​ሥ​ታት ገደለ።
11የአ​ሞ​ራ​ው​ያ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፥
የባ​ሳ​ን​ንም ንጉሥ ዐግን፥
የከ​ነ​ዓ​ንን ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ገደለ፤
12ርስት ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም
ለሕ​ዝቡ#ግእዝ “ገብሩ” ይላል። ለእ​ስ​ራ​ኤል ርስት አድ​ርጎ ሰጠ።
13አቤቱ፥ ስምህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው፥
መታ​ሰ​ቢ​ያ​ህም ለልጅ ልጅ ነው፤
14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ይፈ​ር​ዳ​ልና፥
ባሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያጽ​ና​ና​ልና።#ግእዝ “ስለ​ባ​ሪ​ያ​ዎቹ ይነ​ጋ​ገ​ራል” ይላል።
15የአ​ሕ​ዛብ ጣዖ​ታት የብ​ርና የወ​ርቅ፥
የሰው እጅ ሥራ ናቸው።
16አፍ አላ​ቸው፥ ግን አይ​ና​ገ​ሩም፤
ዐይን አላ​ቸው፥ ግን አያ​ዩም፤
17ጆሮ አላ​ቸው፥ ግን አይ​ሰ​ሙም፤
አፍ​ንጫ አላ​ቸው፥ ግን አያ​ሸ​ቱም፤
እጅ አላ​ቸው፥ ግን አይ​ዳ​ስ​ሱም፤
እግር አላ​ቸው፥ ግን አይ​ሄ​ዱም፤
በጕ​ሮ​ሮ​አ​ቸው አይ​ና​ገ​ሩም፥#በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. “አፍ​ንጫ አላ​ቸው ... በጕ​ሮ​ሮ​አ​ቸው አይ​ና​ገ​ሩም” እስ​ከ​ሚ​ለው ድረስ የለም።
እስ​ት​ን​ፋ​ስም በአ​ፋ​ቸው የለም።
18የሚ​ሠ​ሩ​አ​ቸው ሁሉ፥
የሚ​ታ​መ​ኑ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ እንደ እነ​ርሱ ይሁኑ።
19የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤
የአ​ሮን ወገ​ኖች ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤
20የሌዊ ወገ​ኖች ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈ​ሩት ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት።
21በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ያ​ድር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር
በጽ​ዮን የተ​መ​ሰ​ገነ ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ