መዝሙረ ዳዊት 135
135
ሃሌ ሉያ።
1እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፥
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና።
2የአማልክትን አምላክ አመስግኑ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና።
3የጌቶችን ጌታ አመስግኑ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
4እርሱ ብቻውን ታላቅ ተአምራትን ያደረገ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
5ሰማያትን በጥበቡ የሠራ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
6ምድርን በውኃ ላይ ያጸና፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
7ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
8ለፀሐይ ቀንን ያስገዛው፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
9ለጨረቃና ለከዋክብት ሌሊትን ያስገዛቸው፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
10ከበኵራቸው ጋር ግብፅን የገደለ፥
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
11እስራኤልን ከመካከላቸው ያወጣ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
12በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
13የኤርትራን ባሕር ፈጽሞ የከፈለ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
14እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
15ፈርዖንንና ሠራዊቱን በኤርትራ ባሕር ውስጥ የጣለ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
16ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
ከዓለት ውኃን ያፈለቀ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤#“ከዓለት ውኃን ያፈለቀ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና” የሚለው በዕብ. የለም።
17ታላላቅ ነገሥታትን የገደለ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
18ጽኑዓን ነገሥታትን የገደለ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
19የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፥
20የባሳንን ንጉሥ ዐግን፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
21ርስት ምድራቸውን
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፥
ለባሪያው ለእስራኤል ርስት አድርጎ የሰጠ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
22እግዚአብሔር እኛን በመዋረዳችን ዐስቦናልና፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
23ከጠላቶቻችንም እጅ አድኖናልና፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
24ለሥጋ ሁሉ ምግብን የሚሰጥ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና።
25የሰማይን አምላክ አመስግኑ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 135: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ