መዝሙረ ዳዊት 136
136
1በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን፤
ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን።
2በአኻያ ዛፎችዋ ላይ በገናዎቻችንን ሰቀልን።
3የማረኩን በዚያ የዝማሬ ቃል ጠይቀውናልና፥
የወሰዱንም፥ “የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን” አሉን።
4የእግዚአብሔርን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን?
5ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ብረሳሽ፥ ቀኜ ትርሳኝ።
6ባላስብሽ፥ ምላሴ በጕሮሮዬ ይጣበቅ፤
ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ።
7አቤቱ፥ በኢየሩሳሌም ቀን፦
“እስከ መሠረቷ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ” ያሉአትን የኤዶምን ልጆች ዐስብ።
8አንቺ ወራዳ የባቢሎን ልጅ ሆይ፥
ስለ ተበቀልሽን የሚበቀልሽ ብፁዕ ነው።
9ሕፃናቶችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው ብፁዕ ነው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 136: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ