መዝሙረ ዳዊት 127
127
የመዓርግ መዝሙር።
1እግዚአብሔርን የሚፈሩት ሁሉ፥
በመንገዶቹም የሚሄዱ ብፁዓን ናቸው።
2የድካምህን ፍሬ ትመገባለህ፤
ብፁዕ ነህ፥ መልካምም ይሆንልሃል።
3ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች፤
ልጆችህም በማዕድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወይራ ተክል ይሆናሉ።
4እነሆ፥ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል።
5እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ፤
በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥
የኢየሩሳሌምን መልካምነት ታያለህ።
6የልጆችህንም ልጆች ታያለህ።
በእስራኤል ላይ ሰላም ይሁን።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 127: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ