የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 126

126
የመ​ዓ​ርግ መዝ​ሙር።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትን ካል​ሠራ፥
ቤትን የሚ​ሠሩ በከ​ንቱ ይደ​ክ​ማሉ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​ማን ካል​ጠ​በቀ፥
የሚ​ጠ​ብቁ በከ​ንቱ ይተ​ጋሉ።
2በማ​ለዳ መገ​ሥ​ገ​ሣ​ች​ሁም ከንቱ ነው።
ለወ​ዳ​ጆቹ እን​ቅ​ል​ፍን በሰጠ ጊዜ፥
እና​ንተ የመ​ከ​ራን እን​ጀራ የም​ት​በሉ፥
ከተ​ቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​በት ተነሡ።
3እነሆ፥ ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ ናቸው፥
የሆ​ድም ፍሬ የእ​ርሱ ዋጋ ነው።
4በኀ​ያል እጅ እን​ዳሉ ፍላ​ጾች፥
የተ​ጣሉ ሰዎች#ዕብ. “የጐ​ል​ማ​ሳ​ነት” ይላል። ልጆች እን​ዲሁ ናቸው።
5ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ ምኞ​ቱን የሚ​ፈ​ጽም ሰው ብፁዕ ነው፤
ጠላ​ቶ​ቹን በአ​ደ​ባ​ባይ በተ​ና​ገረ ጊዜ እርሱ አያ​ፍ​ርም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ