መዝሙረ ዳዊት 125
125
የመዓርግ መዝሙር።
1እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥
እጅግ ደስተኞች ሆንን።
2በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን ሞላ፥
አንደበታችንም ሐሤትን አደረገ፤
በዚያን ጊዜ አሕዛብ፦
“እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገላቸው” አሉ።
3 # በመዝ. 125 ቍ. 3 ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገልን” የሚል ይጨምራል። ደስተኞችም ሆን።
4አቤቱ፥ በአዜብ እንዳሉ ፈሳሾች
ምርኮአችንን መልስ።
5በልቅሶ የሚዘሩ በደስታ ይሰበስባሉ።
6በሄዱ ጊዜ፥ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ፤
በተመለሱ ጊዜ ግን ነዶአቸውን ተሸክመው ደስ እያላቸው ይመጣሉ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 125: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ