መዝሙረ ዳዊት 124
124
የመዓርግ መዝሙር።
1በእግዚአብሔር የታመኑ እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው፥
በኢየሩሳሌም የሚኖር ለዘለዓለም አይታወክም።
2ተራሮች ይከቧታል፥
ከዛሬ ጀምሮ ለዘለዓለም
እግዚአብሔር ሕዝቡን ይመግባል።#ዕብ. “በሕዝቡ ዙሪያ ነው” ይላል።
3ጻድቃን እጃቸውን በዐመፃ እንዳይዘረጉ
እግዚአብሔር የኃጥኣንን በትር በጻድቃን ዕጣ ላይ አይተውምና።
4አቤቱ፥ ለቸሮች፥ ልባቸውም ለቀና መልካምን አድርግ።
5ወደ ጠማማነት የሚመለሱትን ግን
ዐመፃን ከሚሠሩት ጋር እግዚአብሔር ይወስዳቸዋል።
ሰላም በእስራኤል ላይ ይሁን።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 124: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ