መዝሙረ ዳዊት 123
123
የዳዊት የመዓርግ መዝሙር።
1እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን
እስራኤል እንዲህ ይበል፦
2እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን
ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥
3የመዓት ቍጣቸውን በላያችን ባነሡ ጊዜ፥
ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር ብዬ በተጠራጠርሁ ነበር፥
4በውኃ ባሰጠሙን ነበር ብዬ በተጠራጠርሁ ነበር፤
5ነፍሳችንም ከጐርፍ አመለጠች፤
ነፍሳችን ከክርክር ውኃ አመለጠች፤
6 # ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይመስገን” ይላል። ወደ ከባቢ ወጥመዳቸው ያላገባን እግዚአብሔር ይመስገን።
7ሰውነታችን ግን እንደ ወፍ ከአዳኝ ወጥመድ አመለጠች፤
ወጥመድ ተሰበረች፥ እኛ ግን ዳን።
8ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በፈጠረ
በእግዚአብሔር ስም ነው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 123: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ