መዝሙረ ዳዊት 122
122
የመዓርግ መዝሙር።
1በሰማይ የምትኖር ሆይ፥ ዐይኖቻችንን ወደ አንተ አነሣን።#ዕብ. “አነሣሁ” ይላል።
2እነሆ፥ የባሪያዎች ዐይኖች ወደ ጌቶቻቸው እጅ እንደ ሆኑ፥
የባሪያዪቱም ዐይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደ ሆነ፥
እንዲሁም ይቅር እስከሚለን ድረስ
ዐይኖቻችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ናቸው።
3ማረን፥ አቤቱ፥ ማረን፤
ስድብን እጅግ ጠግበናልና፤
4የባለጠጎችን ስድብና የትዕቢተኞችን ውርደት
ነፍሳችን እጅግ ጠገበች።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 122: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ