መዝሙረ ዳዊት 121
121
የዳዊት የመዓርግ መዝሙር።
1ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ስላሉኝ ደስ አለኝ።
2ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግሮቻችን በአደባባዮችሽ ቆሙ።
3ኢየሩሳሌምስ እንደ ከተማ የታነጸች ናት።
4እንደ እርሷ ያሉት በአንድነት ከእርሷ ጋር ናቸው።
አቤቱ፥ ለስምህ ይገዙ ዘንድ፥
ለእስራኤል ምስክር የሚሆኑ
የእግዚአብሔር ወገኖች አሕዛብ ወደዚያ ይወጣሉና።
5ለመፍረድ ዙፋኖቻቸውን በዚያ አስቀምጠዋልና፥
የዳዊት ቤት ዙፋኖች።
6የኢየሩሳሌም ደኅንነትዋን፥ ተነጋገሩ።
ስምህን ለሚወድዱ ደስታቸው ነው።
7በኀይልህ ሰላም ይሁን፥
በክብርህ ቦታ ደስታ አለ።
8ስለ ወንድሞቼና ስለ ባልንጀሮቼ ስለ አንቺም፥
ሰላምን ይናገራሉ።
9ስለ አምላኬ ስለ እግዚአብሔር ቤት
ደኅንነትሽን ፈለግሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 121: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ