መዝሙረ ዳዊት 120
120
የመዓርግ መዝሙር።
1ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፤
ረድኤቴ ከወዴት ይምጣ?
2ረድኤቴ ሰማይና ምድርን ከፈጠረ
ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
3ለእግሮችህ ሁከትን አይሰጣቸውም፤
የሚጠብቅህም አይተኛም።
4እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም፥ አያንቀላፋምም።
5እግዚአብሔር ይጠብቅህ፥
እግዚአብሔርም በቀኝ እጁ ይጋርድህ።
6ፀሐይ በቀን አያቃጥልህ፤ ጨረቃም በሌሊት።
7እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅህ፥
እግዚአብሔር ነፍስህንም ይጠብቃት።
8ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም
እግዚአብሔር መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቅ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 120: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ