መዝ​ሙረ ዳዊት 120

120
የመ​ዓ​ርግ መዝ​ሙር።
1ዐይ​ኖቼን ወደ ተራ​ሮች አነ​ሣሁ፤
ረድ​ኤቴ ከወ​ዴት ይምጣ?
2ረድ​ኤቴ ሰማ​ይና ምድ​ርን ከፈ​ጠረ
ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው።
3ለእ​ግ​ሮ​ችህ ሁከ​ትን አይ​ሰ​ጣ​ቸ​ውም፤
የሚ​ጠ​ብ​ቅ​ህም አይ​ተ​ኛም።
4እነሆ፥ እስ​ራ​ኤ​ልን የሚ​ጠ​ብቅ አይ​ተ​ኛም፥ አያ​ን​ቀ​ላ​ፋ​ምም።
5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ብ​ቅህ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀኝ እጁ ይጋ​ር​ድህ።
6ፀሐይ በቀን አያ​ቃ​ጥ​ልህ፤ ጨረ​ቃም በሌ​ሊት።
7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከክፉ ሁሉ ይጠ​ብ​ቅህ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነፍ​ስ​ህ​ንም ይጠ​ብ​ቃት።
8ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መው​ጣ​ት​ህ​ንና መግ​ባ​ት​ህን ይጠ​ብቅ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ