መዝ​ሙረ ዳዊት 119

119
የመ​ዓ​ርግ መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ በተ​ጨ​ነ​ቅሁ ጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ሰማ​ኸ​ኝም።
2ከዐ​መ​ፀኛ ከን​ፈር፥ ከሸ​ን​ጋ​ይም አን​ደ​በት፥ አቤቱ፥ ነፍ​ሴን አድ​ናት።
3ስለ ሽን​ገላ አን​ደ​በት ምንን ይሰ​ጡ​ሃል?
ምንስ ይጨ​ም​ሩ​ል​ሃል?
4እንደ በረሃ ቋያ የኀ​ያል ፍላ​ጾች የተ​ሳሉ ናቸው።
5መኖ​ሪ​ያዬ የራቀ እኔ ወዮ​ልኝ፤
በዘ​ላን ድን​ኳ​ኖች አደ​ርሁ።
6ሰላ​ምን ከሚ​ጠሉ ጋር
ነፍሴ ብዙ ጊዜ ታገ​ሠች።
7እኔ ሰላ​ማዊ ስሆን
በተ​ና​ገ​ር​ኋ​ቸው ጊዜ በከ​ንቱ ይጠ​ሉ​ኛል።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ