የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 128

128
የመ​ዓ​ርግ መዝ​ሙር።
1እስ​ራ​ኤል እን​ዲህ ይበል፥ “ከት​ን​ሽ​ነቴ ጀምሮ ሁል​ጊዜ ተሰ​ለ​ፉ​ብኝ፤
2ከት​ን​ሽ​ነቴ ጀምሮ ሁል​ጊዜ ተሰ​ለ​ፉ​ብኝ፤
ነገር ግን አል​ቻ​ሉ​ኝም።
3ኃጥ​ኣን በጀ​ር​ባዬ ላይ መቱኝ፥
ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም አበ​ዙ​አት።”
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነው፤
የኃ​ጥ​ኣ​ንን አን​ገ​ታ​ቸ​ውን#ግእዝ “አሕ​ዳ​ፊ​ሆሙ” ይላል። ቈረጠ።
5ጽዮ​ንን የሚ​ጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥
ወደ ኋላ​ቸ​ውም ይመ​ለሱ።
6በሰ​ገ​ነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፥
ሳይ​ነ​ቀል እን​ደ​ሚ​ደ​ርቅ፥
7ለሚ​ያ​ጭ​ደው እጁን፥
ነዶ​ዎ​ቹን ለሚ​ሰ​በ​ስ​ብም እቅ​ፉን እን​ደ​ማ​ይ​ሞላ ይሁኑ።
8በመ​ን​ገ​ድም የሚ​ያ​ልፉ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከት በእ​ና​ንተ ላይ ይሁን፤
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እን​መ​ር​ቃ​ች​ኋ​ለን” አይ​በሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ