የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 127

127
የመ​ዓ​ርግ መዝ​ሙር።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩት ሁሉ፥
በመ​ን​ገ​ዶ​ቹም የሚ​ሄዱ ብፁ​ዓን ናቸው።
2የድ​ካ​ም​ህን ፍሬ ትመ​ገ​ባ​ለህ፤
ብፁዕ ነህ፥ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ል​ሃል።
3ሚስ​ትህ በቤ​ትህ እል​ፍኝ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ያ​ፈራ ወይን ትሆ​ና​ለች፤
ልጆ​ች​ህም በማ​ዕ​ድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወ​ይራ ተክል ይሆ​ናሉ።
4እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው እን​ዲህ ይባ​ረ​ካል።
5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጽ​ዮን ይባ​ር​ክህ፤
በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ፥
የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መል​ካ​ም​ነት ታያ​ለህ።
6የል​ጆ​ች​ህ​ንም ልጆች ታያ​ለህ።
በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ሰላም ይሁን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ