መጽሐፈ ምሳሌ 7
7
1ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ጠብቅ፥
ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽግ።
2ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርን አክብረው ትጸናለህም።
ከእርሱ በቀር ሌላውን አትፍራ፥
ከእርሱ በቀር የሚገድልህም የሚያድንህም የለምና።#“ከእርሱ በቀር የሚገድልህም የሚያድንህም የለምና” የሚለው በግእዝ ብቻ ነው።
ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ፤
ቃሌንም እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቅ፤
3በጣቶችህ እሰራቸው፤
በልብህ ጽላትም ጻፋቸው።
4ጥበብን፦ “አንቺ እኅቴ ነሽ” በላት፥
ማስተዋልንም፦ “ወዳጄ” ብለህ ጥራት፥
5ከባዕድና ከክፉ ሴት
ዋዛ ነገርንም ከምታመጣብህ ትጠብቅህ ዘንድ።
ስለ አመንዝራ ሴት አታላይነት
6በቤትWa መስኮት ሆና ወደ ዐደባባይ ትመለከታለችና፤
7ከአላዋቂዎች ወጣቶች መካከል ከዕውቅት ድሃ የሆነውን ጐልማሳ ብታይ፥
8በቤቷም አቅራቢያ ባለው መንገድ ሲሄድ ሲናገርም፤
9ማታ ሲመሽ፥ ውድቅትም ሲሆን፥
በሌሊት በጽኑ ጨለማ፥
10የምንዝር ጌጥ ያላት የጐልማሶችን ልብ እንዲሰቀል የምታደርግ ሴት
ያንጊዜ ትገናኘዋለች።
እርስዋ የምትበርር መዳራትንም የምትወድ ናት።
11ሁከተኛና አበያ ናት፥
እግሮችዋም በቤቷ አያርፉም፥
12አንድ ጊዜ በጎዳና፥ በሌላ ጊዜም በአደባባይ፥
በማዕዘኑም ሁሉ ታደባለች።
13ያዘችውም ሳመችውም፤
ፊቷም ያለ እፍረት ሆኖ እንዲህ አለችው፦
14“የፍቅሬ መሥዋዕት ነው፤
ዛሬ ስእለቴን እሰጣለሁ።
15ስለዚህ እንድገናኝህ መጣሁ፥
ፊትህንም ለማየት ስሻ አገኘሁህ።
16በአልጋዬ ላይ ማለፊያ ሰርፍ ዘርግቼበታለሁ፥
የግብፅንም ሸመልመሌ ምንጣፍ።
17በመኝታዬ ከርቤንና ዓልሙን ቀረፋም ረጭቼበታለሁ።
18ና፥ እስኪነጋ ድረስ በፍቅር እንርካ።
በመልካም መተቃቀፍም ደስ ይበለን።
19ባለቤቴ በቤቱ የለምና፥
ወደ ሩቅ መንገድ ሄዶአልና፤
20በእጁም የወርቅ ከረጢት ይዞአል፤
ወደ ቤቱ ቢመለስም ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው።”
21በብዙ ጨዋታዋ እንዲስት ታደርገዋለች፤
በከንፈርዋ ወጥመድም ትጐትተዋለች።
22እርሱ አንገቱን ደፍቶ ይከተላታል፥
ለመታረድ እንደሚነዳ በሬ፥
ወደ እስራት እንደሚሄድ ውሻ፥
ሆዱ እንደ ተወጋ ዋሊያ፥
23ወደ ወጥመድ እንደሚቸኩል ዎፍ፥
ሳያውቅም ለነፍሱ ጥፋት እንደሚሮጥ።
24ልጄ ሆይ፥ አሁን እንግዲህ ስማኝ፥
ወደ አፌ ቃል አድምጥ።
25ልብህ ወደ መንገድዋ አያዘንብል፤
በጎዳናዋ አትሳት።
26ብዙዎችን ወግታ አስታለች፤
እርስዋም የገደለቻቸው ቍጥር የላቸውም።
27ቤቷ ወደ ሞት ጓዳ የሚያወርድ
የሲኦል መንገድ ነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 7: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ