የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነህ​ምያ 6

6
በነ​ህ​ምያ ላይ የተ​ደ​ረገ ሴራ
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ቅጥ​ሩን እንደ ሠራሁ፥ ከፍ​ራ​ሹም አን​ዳች እን​ዳ​ል​ቀ​ረ​በት ሰን​ባ​ላ​ጥና ጦቢያ ዓረ​ባ​ዊ​ውም ጌሳም የቀ​ሩ​ትም ጠላ​ቶ​ቻ​ችን ሰሙ፤ ነገር ግን እስ​ከ​ዚያ ጊዜ ድረስ በበ​ሮቹ ውስጥ ሳን​ቃ​ዎ​ቹን አላ​ቆ​ም​ሁም ነበር። 2ሰን​ባ​ላ​ጥና ጌሳም፥ “መጥ​ተህ በኦኖ ቈላ ውስጥ ባሉት መን​ደ​ሮች እን​ገ​ናኝ” ብለው ላኩ​ብኝ፤ ነገር ግን ክፉ ያደ​ር​ጉ​ብኝ ዘንድ ይመ​ክሩ ነበር። 3እኔም እን​ዲህ ስል መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላክ​ሁ​ባ​ቸው፥ “እኔ ታላቅ ሥራ እሠ​ራ​ለሁ፤ እወ​ር​ድም ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም። ስለ​ምን ወደ እና​ንተ በመ​ም​ጣ​ቴና በመ​ው​ረዴ ሥራው ይታ​ጐ​ላል? ሥራ​ውን እንደ ፈጸ​ምሁ እመ​ጣ​ለሁ።” 4እን​ዲ​ህም ቃል አራት ጊዜ#“አራት ጊዜ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ላኩ​ብኝ፤ እኔም እንደ ፊተ​ኛው ቃል መለ​ስ​ሁ​ላ​ቸው። 5ሰን​ባ​ላ​ጥም እንደ ፊተ​ኛው ብላ​ቴ​ና​ውን አም​ስ​ተኛ ጊዜ#“አም​ስ​ተኛ ጊዜ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ ሊ. የለም። ላከ​ብኝ፤ በእ​ጁም ውስጥ እን​ዲህ የሚል ግልጥ ደብ​ዳቤ ነበረ፦ 6“አን​ተና አይ​ሁድ ዓመፃ እን​ድ​ታ​ስቡ፥ ስለ​ዚ​ህም ቅጥ​ሩን እን​ድ​ት​ሠራ፥ ንጉ​ሣ​ቸ​ውም ትሆን ዘንድ እን​ድ​ት​ወ​ድድ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ተሰ​ም​ቶ​አል። 7ደግ​ሞም፦ ንጉሥ በይ​ሁዳ አለ ብለው ስለ አንተ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይና​ገሩ ዘንድ ነቢ​ያ​ትን አቁ​መ​ሃል፤ አሁ​ንም ለን​ጉሡ ይህን ቃል ያወ​ሩ​ለ​ታል፤ እን​ግ​ዲህ መጥ​ተህ በአ​ን​ድ​ነት እን​ማ​ከር።” 8እኔም፥ “አንተ ከል​ብህ ፈጥ​ረ​ኸ​ዋል እንጂ እንደ ተና​ገ​ር​ኸው ነገር አይ​ደ​ለም” ብዬ ላክ​ሁ​በት። 9እነ​ር​ሱም ሁሉ ሥራው እን​ዳ​ይ​ፈ​ጸም፥ “እጃ​ቸው ይደ​ክ​ማል” ብለው አስ​ፈ​ራ​ሩን፤ ስለ​ዚ​ህም እጆ​ችን አበ​ረ​ታሁ።#ዕብ. “አሁ​ንም አም​ላኬ ሆይ እጆ​ችን አበ​ርታ” ይላል።
10እኔም ወደ መሔ​ጣ​ብ​ኤል ልጅ ወደ ዶልያ ልጅ ወደ ሴሜይ ቤት ገባሁ፤ እር​ሱም ተዘ​ግቶ ነበ​ርና፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ እን​ግባ፤ የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንም ደጆች እን​ዝጋ፤ እነ​ርሱ በሌ​ሊት ይገ​ድ​ሉህ ዘንድ ይመ​ጣ​ሉና” አለኝ። 11እኔም፥ “እንደ እኔ ያለ ሰው የሸ​ሸና፥#“እንደ እኔ ያለ ሰው የሸ​ሸና” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ነፍ​ሱ​ንስ ያድን ዘንድ ወደ መቅ​ደስ የገባ ማን ነው? እኔስ አል​ገ​ባም” አል​ሁት። 12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልኮት እን​ዳ​ል​ነ​በረ፥ በእኔ ላይ ግን ትን​ቢት እንደ ተና​ገረ፥ እነሆ፥ ዐወ​ቅሁ፤ ጦብ​ያና ሰን​ባ​ላ​ጥም ገዝ​ተ​ውት ነበር። 13ይህ​ንም ነገር አደ​ር​ግና እበ​ድል ዘንድ፥ በእ​ኔም ላይ ክፋት እን​ዲ​ና​ገ​ሩና እን​ዲ​ያ​ላ​ግጡ ያስ​ፈ​ራ​ራኝ ዘንድ ተገ​ዝቶ ነበር። 14አም​ላኬ ሆይ፥ ስለ​ዚህ ሥራ​ቸው ጦቢ​ያ​ንና ሰን​ባ​ላ​ጥን፥ ነቢ​ይ​ቱ​ንም ኖዓ​ድ​ያን ያስ​ፈ​ራ​ሩኝ ዘንድ የፈ​ለ​ጉ​ትን፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ነቢ​ያት አስብ።
የቅ​ጥሩ ግንብ ሥራ መፈ​ጸም
15ቅጥ​ሩም በኤ​ሉል ወር በሃያ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በአ​ምሳ ሁለት ቀን ውስጥ ተጨ​ረሰ። 16እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ችን ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ በዙ​ሪ​ያ​ችን የነ​በሩ አሕ​ዛብ ሁሉ ፈሩ፤ አይ​ተ​ውም እጅግ ተደ​ና​ገጡ፤ ይህም ሥራ በአ​ም​ላ​ካ​ችን እንደ ተፈ​ጸመ አወቁ። 17በዚ​ያም ወራት ብዙ የይ​ሁዳ አለ​ቆች ወደ ጦብያ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ችን ይልኩ ነበር፤ የጦ​ብ​ያም ደብ​ዳ​ቤ​ዎች ወደ እነ​ርሱ ይመጡ ነበር። 18ጦብያ የአ​ራሄ ልጅ የሴ​ኬ​ንያ አማች ስለ ነበረ፥ ልጁም ዮሐ​ናን የቤ​ራ​ክ​ያን ልጅ የሜ​ሱ​ላ​ምን ሴት ልጅ ስላ​ገባ፥ በይ​ሁዳ ብዙ ሰዎች ከእ​ርሱ ጋር ተማ​ም​ለው ነበ​ርና። 19ደግ​ሞም በፊቴ ስለ እርሱ መል​ካ​ም​ነት ይና​ገሩ ነበር፤ የእ​ር​ሱን ነገር ወደ እኔ ያመጡ ነበር፤ የእ​ኔ​ንም ቃል ወደ እርሱ ይወ​ስዱ ነበር፤ ጦቢ​ያም ሊያ​ስ​ፈ​ራ​ራኝ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ችን ይልክ ነበር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ