ለሕዝቡም ቃሉን ነግሮ ከፈጸመ በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ገባ። አንድ የመቶ አለቃም ነበረ፤ አገልጋዩም ታሞ ሊሞት ቀርቦ ነበር፤ እርሱም በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነበር። የጌታችን የኢየሱስንም ነገር በሰማ ጊዜ፥ መጥቶ አገልጋዩን እንዲያድንለት ይማልዱት ዘንድ የአይሁድን ሽማግሎች ወደ እርሱ ላከ። ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስም መጥተው ማለዱት፤ እንዲህም አሉት፥ “ፈጥነህ ውረድ፤ ይህን ልታደርግለት ይገባዋልና። እርሱ ወገናችንን ይወዳልና፤ ምኵራባችንንም ሠርቶልናልና።” ጌታችን ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ሄደ፤ ወደ ቤቱም በቀረበ ጊዜ፥ የመቶ አለቃዉ ወዳጆቹን እንዲህ ብሎ ላከ፥ “አቤቱ፥ አትድከም፤ ከቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝምና። እኔም ወደ አንተ ልመጣ አይገባኝም፤ ነገር ግን በቃልህ እዘዝ፤ ብላቴናዬም ይድናል። እኔም እኮ ገዢ ሰው ነኝ፤ ወታደሮችም አሉኝ፤ አንዱን ሂድ ብለው ይሄዳል፤ ሌላውንም ና ብለው ይመጣል፤ አገልጋዬንም እንዲህ አድርግ ብለው ያደርጋል።” ጌታችን ኢየሱስም ይህን ከእርሱ በሰማ ጊዜ አደነቀው፤ ዘወር ብሎም ይከተሉት ለነበሩት ሕዝብ፥ “እላችኋለሁ፥ በእስራኤልስ እንኳ እንዲህ ያለ እምነት ያለው ሰው አላገኘሁም” አላቸው። የተላኩትም በተመለሱ ጊዜ ብላቴናውን ድኖ አገኙት።
የሉቃስ ወንጌል 7 ያንብቡ
ያዳምጡ የሉቃስ ወንጌል 7
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሉቃስ ወንጌል 7:1-10
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች